Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 5:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በታ​ቦ​ቷም ውስጥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ ምድር በወጡ ጊዜ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን ባደ​ረገ ጊዜ ሙሴ በኮ​ሬብ ካስ​ቀ​መ​ጣ​ቸው ከሁ​ለቱ ጽላት በቀር ምንም አል​ነ​በ​ረ​ባ​ትም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እስራኤላውያን ከግብጽ ከወጡ በኋላ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋራ ኪዳን ባደረገ ጊዜ፣ ሙሴ በኮሬብ ተራራ በውስጡ ካስቀመጣቸው ከሁለቱ ጽላት በቀር በታቦቱ ውስጥ ምንም አልነበረም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በታቦቱም ውስጥ የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ፥ ጌታም ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን ባደረገ ጊዜ ሙሴ በኮሬብ ካስቀመጣቸው ከሁለቱ ጽላቶች በቀር ምንም አልነበረበትም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እስራኤላውያን ከግብጽ እንደ ወጡ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን በገባ ጊዜ ሙሴ በሲና ተራራ በቃል ኪዳኑ ታቦት ውስጥ ካስቀመጣቸው ከሁለቱ ጽላቶች በቀር በታቦቱ ውስጥ ሌላ ነገር አልነበረም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 በታቦቱም ውስጥ የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ፥ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን ባደረገ ጊዜ ሙሴ በኮሬብ ካስቀመጣቸው ከሁለቱ ጽላቶች በቀር ምንም አልነበረበትም።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 5:10
14 Referencias Cruzadas  

በው​ስ​ጥ​ዋም የወ​ርቅ ማዕ​ጠ​ን​ትና ሁለ​ን​ተ​ና​ዋን በወ​ርቅ የለ​በ​ጡ​አት፥ የኪ​ዳን ታቦት፥ መና ያለ​ባት የወ​ርቅ መሶ​ብና የለ​መ​ለ​መ​ችው የአ​ሮን በትር፥ የኪ​ዳ​ኑም ጽላት ነበ​ሩ​ባት።


ከሕ​ዝ​ቡም ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ያደ​ረ​ገው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ኪዳን ያለ​ባ​ትን ታቦት በዚ​ያው ውስጥ አኖ​ርሁ።”


አሁ​ንም ቃሌን በእ​ው​ነት ብት​ሰሙ፥ ኪዳ​ኔ​ንም ብት​ጠ​ብቁ፥ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ የተ​መ​ረጠ ርስት ትሆ​ኑ​ል​ኛ​ላ​ችሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኮ​ሬብ ካደ​ረ​ገው ቃል ኪዳን ሌላ በሞ​ዓብ ምድር ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጋር ያደ​ር​ገው ዘንድ ሙሴን ያዘ​ዘው የቃል ኪዳኑ ቃሎች እነ​ዚህ ናቸው።


ሙሴም ጽላ​ቱን ወስዶ በታ​ቦቱ ውስጥ አኖ​ረው፤ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም በታ​ቦቱ ቀለ​በ​ቶች ውስጥ አደ​ረገ፤ የስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ው​ንም በታ​ቦቱ ላይ አኖ​ረው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ሁለት የድ​ን​ጋይ ጽላት እንደ ፊተ​ኞቹ አድ​ር​ገህ ቅረጽ፤ ወደ እኔም ወደ ተራራ ውጣ፤ በሰ​በ​ር​ሃ​ቸው በፊ​ተ​ኞቹ ጽላት የነ​በ​ሩ​ትን ቃላት እጽ​ፍ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ወደ ሰፈሩ ሲቀ​ርብ ጥጃ​ው​ንም ዘፈ​ኑ​ንም አየ፤ የሙ​ሴም ቍጣ ተቃ​ጠለ፤ እነ​ዚ​ያ​ንም ሁለ​ቱን ጽላት ከእጁ ጥሎ ከተ​ራ​ራው በታች ሰበ​ራ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር በሲና ተራራ የተ​ና​ገ​ረ​ውን በፈ​ጸመ ጊዜ ሁለ​ቱን የም​ስ​ክር ጽላት፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጣት የተ​ጻ​ፈ​ባ​ቸ​ውን የድ​ን​ጋይ ጽላት ለሙሴ ሰጠው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios