2 ዜና መዋዕል 35:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 ከነቢዩም ከሳሙኤል ዘመን ጀምሮ እንደዚህ ያለ ፋሲካ በእስራኤል ዘንድ ከቶ አልተደረገም፤ ከእስራኤልም ነገሥታት ሁሉ ኢዮስያስና ካህናቱ፥ ሌዋውያኑም፥ በዚያም የተገኙ የይሁዳና የእስራኤል ሰዎች ሁሉ፥ በኢየሩሳሌምም የሚኖሩት እንዳደረጉት ያለ ፋሲካ ያደረገ የለም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም18 ከነቢዩ ሳሙኤል ዘመን ጀምሮ እንዲህ ያለ ፋሲካ በእስራኤል ዘንድ ተከብሮ አያውቅም፤ ኢዮስያስ ከካህናቱ፣ ከሌዋውያኑ፣ ከመላው ይሁዳና ከእስራኤል፣ በዚያ ከነበሩትም ከኢየሩሳሌም ሰዎች ጋራ እንዳከበረው አድርጎ ያከበረ አንድም የእስራኤል ንጉሥ የለም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 ከነቢዩ ከሳሙኤል ዘመን ጀምሮ እንደዚህ ያለ ፋሲካ በእስራኤል ዘንድ ከቶ ተከብሮ አያውቅም፤ ከእስራኤልም ነገሥታት ሁሉ ኢዮስያስና ካህናቱ፥ ሌዋውያኑም፥ በዚያም የተገኙ የይሁዳና የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ፥ በኢየሩሳሌምም የሚኖሩት እንዳከበሩት ያለ ፋሲካ ያከበረ የለም። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 ከነቢዩ ሳሙኤል ዘመን ጀምሮ የፋሲካ በዓል ይህን በመሰለ ሁኔታ ከቶ ተከብሮ አያውቅም፤ ንጉሥ ኢዮስያስ፥ ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ የይሁዳ፥ የእስራኤልና የኢየሩሳሌም ሕዝብ የፋሲካን በዓል አሁን ባከበሩት ዐይነት ከዚህ በፊት ከነበሩት ነገሥታት መካከል፥ አንዱ እንኳ አክብሮ አያውቅም፤ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 ከነቢዩ ከሳሙኤል ዘመን ጀምሮ እንደዚህ ያለ ፋሲካ በእስራኤል ዘንድ ከቶ አልተደረገም፤ ከእስራኤልም ነገሥታት ሁሉ ኢዮስያስና ካህናቱ፥ ሌዋውያኑም፥ በዚያም የተገኙ የይሁዳና የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ፥ በኢየሩሳሌምም የሚኖሩት እንዳደረጉት ያለ ፋሲካ ያደረገ የለም። Ver Capítulo |
ይህም ፋሲካ ኢዮስያስ በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት ተደረገ። 19 ‘ሀ’ ንጉሡ ኢዮስያስ ካህኑ ኬልቅያስ በእግዚአብሔር ቤት ባገኘው መጽሐፍ የተጻፉትን ቃላት ሁሉ ለመጠበቅ አስማተኞችንና ጠንቋዮችን፥ ሟርተኞችንና በኢየሩሳሌም ምድርና በይሁዳ የሚገኙትን ምስሎችና ቃሪያሲም የተባሉ ጣዖታትን በእሳት አቃጠለ። 19 ‘ለ’ እንደ ሙሴ ሕግ ሁሉ በፍጹም ልቡ፥ በፍጹም ነፍሱ፥ በፍጹም ኀይሉ ከእርሱ በፊት ከነበሩት ወደ እግዚአብሔር የተመለሰ የሚመስለው ሰው አልነበረም። ከእርሱም በኋላ የሚመስለው አልተነሣም። 19 ‘ሐ’ ነገር ግን እግዚአብሔር ንጉሥ ምናሴ በይሁዳ ላይ በአደረገውና በአነሣሣው ጥፋት ሁሉ ከአስከተለው ታላቅ ቍጣ አልተመለሰም። 19 ‘መ’ እግዚአብሔርም አለ፥ “እስራኤልን እንዳራቅሁ ይሁዳን ከፊቴ አርቃለሁ። የመረጥኋትንም ከተማ ኢየሩሳሌምንና ስሜ በዚያ ይጠራበታል ያልሁትን ቤት እጥላለሁ።”