27 ከዚህ በኋላ በዳዊት ከተማ በስተውጭው ከግዮን ሰሜናዊ ምዕራብ በሸለቆው ውስጥ እስከ ዓሣ በር መግቢያ ድረስ ቅጥር ሠራ። እስከ ዖፌልም አዞረበት፤ እጅግም ከፍ አደረገው፤ በተመሸጉትም በይሁዳ ከተሞች ሁሉ የጭፍራ አለቆችን አኖረ።