Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 32:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ብዙ ሰዎ​ች​ንም ሰበ​ሰበ፥ “የአ​ሦ​ርም ንጉሥ እን​ዳ​ይ​መ​ጣና ብዙ ውኃ አግ​ኝቶ እን​ዳ​ይ​ጠ​ነ​ክር” ብሎ የውኃ ምን​ጮ​ች​ንና በከ​ተ​ማ​ዪቱ የሚ​ፈ​ስ​ሱ​ትን ወን​ዞች ደፈነ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ብዙ ሰዎችም ተሰብስበው “የአሦር ነገሥታት መጥተው ስለ ምን ብዙ ውሃ ያገኛሉ?” በማለት ምንጮቹን ሁሉና በምድር ውስጥ ለውስጥ ይተላለፍ የነበረውን ውሃ ዘጉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እጅግም ሰዎች ተሰብስበው፦ “የአሦር ነገሥታት መጥተው ብዙ ውኃ ለምን ያገኛሉ?” ብለው ምንጩን ሁሉ፥ በምድርም መካከል ይንዶለዶል የነበረውን ዥረት ደፈኑ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እጅግም ሰዎች ተሰብስበው “የአሦር ነገሥታት መጥተው ብዙ ውኃ ስለ ምን ያገኛሉ?” ብለው ምንጩን ሁሉ፥ በምድርም መካከል ይንዶለዶል የነበረውን ወንዝ ደፈኑ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 32:4
15 Referencias Cruzadas  

ከእ​ር​ሱም ዘንድ ተመ​ልሶ ሁለ​ቱን በሬ​ዎች ወስዶ አረ​ዳ​ቸው፤ ሥጋ​ቸ​ው​ንም በበ​ሬ​ዎቹ ዕቃ ቀቀ​ለው፤ ለሕ​ዝ​ቡም ሰጣ​ቸው፤ በሉም፤ እር​ሱም ተነ​ሥቶ ኤል​ያ​ስን ተከ​ትሎ ሄደ፤ ያገ​ለ​ግ​ለ​ውም ነበር።


ስለ​ዚ​ህም ሰምቶ በሕ​ዝ​ብህ ላይ መፍ​ረድ ይችል ዘንድ፥ መል​ካ​ሙ​ንና ክፉ​ው​ንም ይለይ ዘንድ ለባ​ሪ​ያህ አስ​ተ​ዋይ ልቡና ስጠው፤ አለ​ዚ​ያማ በዚህ በታ​ላቅ ሕዝብ ላይ ይፈ​ርድ ዘንድ ማን ይች​ላል?”


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም በነ​ገሠ በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ዓመት የአ​ሦር ንጉሥ ሰና​ክ​ሬም ወደ ይሁዳ ወደ ተመ​ሸ​ጉት ከተ​ሞች ሁሉ ወጣ፤ ወሰ​ዳ​ቸ​ውም።


ሕዝ​ቅ​ያስ በነ​ገሠ በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመት፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ የኤላ ልጅ ሆሴዕ በነ​ገሠ በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት፥ የአ​ሦር ንጉሥ ስል​ም​ና​ሶር ወደ ሰማ​ርያ ወጣ፤ ከበ​ባ​ትም።


አቤቱ፥ በእ​ው​ነት የአ​ሦር ነገ​ሥት አሕ​ዛ​ብን አጥ​ፍ​ተ​ዋል፤


የቀ​ረ​ውም የሕ​ዝ​ቅ​ያስ ነገር፥ ኀይ​ሉም ሁሉ፥ ኵሬ​ው​ንና መስ​ኖ​ውን እንደ ሠራ፥ ውኃ​ው​ንም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ እን​ዳ​መጣ፥ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት ታሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


ተነ​ሥ​ተ​ውም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የነ​በ​ሩ​ትን መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ችና ለጣ​ዖ​ታት የሚ​ያ​ጥ​ኑ​በ​ትን ዕቃ ሁሉ አስ​ወ​ገዱ፤ በቄ​ድ​ሮ​ንም ወንዝ ጣሉት።


ከእ​ነ​ዚ​ህም ነገ​ሮ​ችና ከዚህ እው​ነት በኋላ የአ​ሦር ንጉሥ ሰና​ክ​ሬም መጥቶ ወደ ይሁዳ ገባ፤ በተ​መ​ሸ​ጉ​ትም ከተ​ሞች ፊት ሰፈረ፤ ሊወ​ስ​ዳ​ቸ​ውም አሰበ።


ከከ​ተ​ማ​ዪቱ በስ​ተ​ውጭ ያለ​ውን የው​ኃ​ውን ምንጭ ይደ​ፍኑ ዘንድ ከአ​ለ​ቆ​ቹና ከኀ​ያ​ላኑ ጋር ተማ​ከረ፤ እነ​ር​ሱም ምክ​ሩን ወደዱ።


ይህም ሕዝ​ቅ​ያስ የላ​ይ​ኛ​ውን የግ​ዮ​ንን ውኃ ምንጭ ደፈነ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ በም​ዕ​ራብ በኩል አቅ​ንቶ አወ​ረ​ደው። ሕዝ​ቅ​ያ​ስም በሥ​ራው ሁሉ ተከ​ና​ወነ።


“አንተ ብቻ​ህን አለቃ ነህን?” ቢሉ​ትም፥ የሔ​ማ​ትን መን​ደር ወሰ​ድሁ ይላል።


በአ​ሮ​ጌው ኵሬ ላለው ውኃ በሁ​ለቱ ቅጥር መካ​ከል መከ​ማቻ ሠራ​ችሁ፤ ይህን ያደ​ረ​ገ​ውን ግን አል​ተ​መ​ለ​ከ​ታ​ች​ሁም፤ ቀድሞ የሠ​ራ​ው​ንም አላ​ያ​ች​ሁም።


የዳ​ዊ​ትም ከተማ ፍራ​ሾች እን​ደ​በዙ አይ​ታ​ች​ኋል፤ የታ​ች​ኛ​ው​ንም ኵሬ ውኃ በከ​ተማ አከ​ማ​ች​ታ​ች​ኋል፤


ከብበው ያስጨንቁሻልና ውኃን ቅጂ፣ አምባሽን አጠንክሪ፣ ወደ ጭቃ ገብተሽ እርገጪ፣ የጡብን መሠሪያ ያዢ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos