Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 31:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በካ​ህ​ና​ቱም ከተ​ሞች ለታ​ላ​ላ​ቆ​ችና ለታ​ና​ና​ሾች ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው ክፍ​ላ​ቸ​ውን በእ​ም​ነት ይሰጡ ዘንድ ኤዶም፥ ብን​ያስ፥ ኢያሱ፥ ሴሚ፥ አማ​ርያ፥ ኮክ​ን​ያስ ከእጁ በታች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ዔድን፣ ሚንያሚን፣ ኢያሱ፣ ሸማያ፣ አማርያና ሴኬንያ በካህናቱ ከተሞች ተገኝተው፣ ለካህናት ወገኖቻቸው ለታላላቆቹም ሆነ ለታናናሾቹ፣ እንደየምድባቸው፣ በማከፋፈሉ ረገድ በታማኝነት ረዱት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 በካህናቱም ከተሞች ለታላላቆችና ለታናናሾች ወንድሞቻቸው በየሰሞናቸው ድርሻቸውን በታማኝነት እንዲሰጡ ዔድን፥ ሚንያሚን፥ ኢያሱ፥ ሸማያ፥ አማርያ፥ ሴኬንያ የቆሬ ረዳቶች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ካህናት በሚኖሩባቸው በሌሎች ከተሞች ቆሬን በታማኝነት የሚረዱ ዔደን፥ ሚንያሚን፥ ኢያሱ፥ ሸማዕያ፥ አማርያና ሸካንያ ተብለው የሚጠሩ ሰዎች ነበሩ፤ እነርሱም በሥራቸው ምድብ መሠረት ምግቡን ወገኖቻቸው ለሆኑ ሌዋውያን በትክክል ያከፋፍሉ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በካህናቱም ከተሞች ለታላላቆችና ለታናናሾች ወንድሞቻቸው በየሰሞናቸው ክፍላቸውን በእምነት ይሰጡ ዘንድ ዔድን፥ ሚንያሚን፥ ኢያሱ፥ ሸማያ፥ አማርያ፥ ሴኬንያ ከእጁ በታች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 31:15
8 Referencias Cruzadas  

እነ​ዚ​ህም ደግሞ በን​ጉሡ በዳ​ዊ​ትና በሳ​ዶቅ በአ​ቤ​ሜ​ሌ​ክም በሌ​ዋ​ው​ያ​ንና በካ​ህ​ናት አባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ፊት፥ ታላ​ላ​ቆች እንደ ታና​ናሽ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው፥ እንደ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው እንደ አሮን ልጆች ዕጣ ተጣ​ጣሉ።


ሁሉም ተካ​ክ​ለው፥ ታና​ሹም ታላ​ቁም፥ ለሰ​ሞ​ና​ቸው ዕጣ ተጣ​ጣሉ እነ​ር​ሱም ፍጹ​ማ​ንና የተ​ማሩ ነበሩ።


የመ​ድ​ረኩ በረ​ኞች ይሆኑ ዘንድ የተ​መ​ረጡ እነ​ዚህ ሁሉ ሁለት መቶ ዐሥራ ሁለት ነበሩ። እነ​ዚህ በመ​ን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው ተቈ​ጠሩ። ዳዊ​ትና ነቢዩ ሳሙ​ኤል ታማ​ኝ​ነ​ታ​ቸ​ውን አይ​ተው በሥ​ራ​ቸው አቆ​ሙ​አ​ቸው።


ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ ከቀ​ዓት ልጆች የአ​ሜ​ሳእ ልጅ መኤ​ትና የዓ​ዛ​ር​ያስ ልጅ ኢዮ​ሔል፥ ከሜ​ራ​ሪም ልጆች የአ​ብዲ ልጅ ቂስና የያ​ሃ​ሌ​ል​ኤል ልጅ ዓዛ​ር​ያስ፥ ከጌ​ድ​ሶ​ንም ልጆች የዛ​ማት ልጅ ዮአ​ክና የዮ​አክ ልጅ ኢዮ​አድ፤


ንጉ​ሡም ሕዝ​ቅ​ያ​ስና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አለቃ ዓዛ​ር​ያስ እንደ አዘዙ ኢዮ​ኤል፥ ዓዛ​ዝያ፥ አና​ኤት፥ ኡሳ​ሄል፥ ኢያ​ሪ​ሞት፥ ኢዮ​ዛ​ብድ፥ ኤል​ሄል፥ ሰማ​ኪያ፥ መሐት፥ በና​ያ​ስና ልጆቹ፥ ከኮ​ክ​ን​ያ​ስና ከወ​ን​ድሙ ከሰ​ሜኢ እጅ በታች ተቈ​ጣ​ጣ​ሪ​ዎች ነበሩ።


የሌ​ዋ​ዊ​ውም የይ​ም​ላእ ልጅ የም​ሥ​ራቁ ደጅ በረኛ ቆሬ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መባና የተ​ቀ​ደ​ሱ​ትን ነገ​ሮች እን​ዲ​ያ​ካ​ፍል ሕዝቡ በፈ​ቃ​ዳ​ቸው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ቀ​ረ​ቡት ላይ ተሾመ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos