Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 30:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ካህ​ናቱ በሚ​በቃ ቍጥር ስላ​ል​ተ​ቀ​ደሱ፥ ሕዝ​ቡም ገና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ስላ​ል​ተ​ሰ​በ​ሰቡ በጊ​ዜው ያደ​ር​ጉት ዘንድ አል​ቻ​ሉም ነበ​ርና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በቂ ካህናት ራሳቸውን ስላልቀደሱና ሕዝቡም ገና በኢየሩሳሌም ስላልተሰበሰቡ፣ በዓሉን በወቅቱ ለማክበር አልቻሉም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ዳሩ ግን በጊዜው ለማክበር አልቻሉም ነበር ምክንያቱም በቊጥር በቂ የሆኑ ካህናት ስላልተቀደሱ፥ ሕዝቡም ገና በኢየሩሳሌም ስላልተሰባሰቡ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 30:3
8 Referencias Cruzadas  

በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ያነጹ ጀመር፤ በዚ​ያ​ውም ወር በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወለል ደረሱ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት በስ​ም​ንት ቀን አነጹ፤ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በዐ​ሥራ ስድ​ስ​ተ​ኛው ቀን ፈጸሙ።


ነገር ግን ካህ​ናቱ ጥቂ​ቶች ነበ​ሩና የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ለመ​ግ​ፈፍ አይ​ች​ሉም ነበር፤ ስለ​ዚ​ህም ሌዋ​ው​ያን በቅን ልብ ከካ​ህ​ናት ይልቅ ይቀ​ደሱ ነበ​ርና ሥራው እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ፥ ካህ​ና​ቱም እስ​ኪ​ቀ​ደሱ ድረስ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ሌዋ​ው​ያን ያግ​ዙ​አ​ቸው ነበር።


በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ወር በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን የፋ​ሲ​ካ​ውን በግ አረዱ፤ ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም ተዘ​ጋጁ ነጹም። ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አመጡ።


ንጉሡ ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ስለ ቍር​ባን ሺህ ወይ​ፈ​ኖ​ች​ንና ሰባት ሺህ በጎ​ችን ለይ​ሁ​ዳና ለጉ​ባ​ኤው ሰጥቶ ነበር፤ አለ​ቆ​ቹም ሺህ ወይ​ፈ​ኖ​ች​ንና ዐሥር ሺህ በጎ​ችን ለጉ​ባ​ኤው ሰጥ​ተው ነበር፤ ከካ​ህ​ናቱ እጅግ ብዙ ተቀ​ድ​ሰው ነበ​ርና።


ነገ​ሩም ንጉ​ሡ​ንና ጉባ​ኤ​ውን ሁሉ ደስ የሚ​ያ​ሰኝ ሆነ።


የፋ​ሲ​ካ​ው​ንም በግ እረዱ፤ እና​ን​ተም ተቀ​ደሱ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሙሴ እጅ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ታደ​ርጉ ዘንድ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ አዘ​ጋጁ።”


ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን ሠርክ ጀም​ራ​ችሁ እስ​ከ​ዚሁ ወር ሃያ አን​ደኛ ቀን ሠርክ ድረስ ቂጣ ትበ​ላ​ላ​ችሁ።


በዚ​ህም ወር እስከ ዐሥራ አራ​ተኛ ቀን ድረስ ጠብ​ቁት፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ሲመሽ ይረ​ዱት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos