Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 12:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ሺህ ሁለት መቶ ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና ስድሳ ሺህ ፈረ​ሰ​ኞ​ችን ይዞ መጣ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ከግ​ብፅ ለመ​ጣው ሕዝብ ቍጥር አል​ነ​በ​ረ​ውም፤ እነ​ር​ሱም የል​ብያ ሰዎች፥ ሞጠ​ግ​ሊ​ያ​ና​ው​ያን፥ የኢ​ት​ዮ​ጵ​ያም ሰዎች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ከግብጽ ዐብረውት የመጡትን ዐሥራ ሁለት ሺሕ ሠረገላዎች፣ ስድሳ ሺሕ ፈረሰኞችና ስፍር ቍጥር የሌላቸውን የሊቢያ፣ የሱኪምና የኢትዮጵያ ወታደሮችን ይዞ፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እርሱም ሺህ ሁለት መቶ ሰረገሎችና ስልሳ ሺህ ፈረሰኞች ይዞ ነበር። ከእርሱም ጋር ከግብጽ ለመጣው ሕዝብ ቍጥር አልነበረውም፤ እነርሱም የልብያ ሰዎች ሱካውያን፥ የኢትዮጵያ ሰዎችም ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እርሱም አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሠረገሎችና ሥልሳ ሺህ ፈረሰኞች ነበሩት፤ በሺሻቅ ጦር ሠራዊት ውስጥ ከእርሱ ጋር ከግብጽ የመጡ ብዛታቸው ሊቈጠር የማይቻል ሊቢያውያን፥ ሱካውያንና ኢትዮጵያውያን ነበሩ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ከእርሱም ጋር ከግብጽ ለመጣው ሕዝብ ቁጥር አልነበረውም፤ እነርሱም የልብያ ሰዎች፥ ሱካውያን፥ የኢትዮጵያ ሰዎችም ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 12:3
15 Referencias Cruzadas  

ኢትዮጵያና ግብጽ የማይቈጠር ኃይልዋ ነበሩ፣ ፉጥና ልብያ ረዳቶችዋ ነበሩ።


ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ው​ያ​ንና የል​ብያ ሰዎች እጅግ ብዙ ሰረ​ገ​ሎ​ችና ፈረ​ሰ​ኞች የነ​በ​ሩ​አ​ቸው እጅግ ታላቅ ጭፍራ አል​ነ​በ​ሩ​ምን? በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ታመ​ንህ በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።


የፈረሰኞችም ጭፍራ ቁጥር ሁለት መቶ ሚሊዮን ነበረ፤ ቁጥራቸውን ሰማሁ።


ኢት​ዮ​ጵ​ያና ፉጥ፥ ሉድም፥ ዓረ​ብም ሁሉ፥ ኩብም፤ ሊብ​ያም፤ ቀር​ጤ​ስም የተ​ደ​ባ​ለቀ ሕዝ​ብም ሁሉ፥ ቃል ኪዳ​ን​ንም የገ​ባ​ችው ምድር ልጆች ከእ​ነ​ርሱ ጋር በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ።


እኔ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መድ​ኀ​ኒ​ትህ ነኝ፤ ግብ​ፅ​ንና ኢት​ዮ​ጵ​ያን ለአ​ንተ ቤዛ አድ​ርጌ፥ ሴዎ​ን​ንም ለአ​ንተ ፋንታ ሰጥ​ቻ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ሳና በይ​ሁዳ ሕዝብ ፊት ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ው​ያ​ንን መታ፤ ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ው​ያ​ንም ሸሹ።


የኢ​ት​ዮ​ጵ​ያም ንጉሥ ዝሪ አንድ ሚሊ​ዮን ሰዎ​ችና ሦስት መቶ ሰረ​ገ​ሎች ይዞ ወጣ​ባ​ቸው፤ ወደ መሪ​ሳም መጣ።


ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ፊት ሸሹ፤ ዳዊ​ትም ከሶ​ር​ያ​ው​ያን ሰባት መቶ ሰረ​ገ​ለ​ኞ​ችን፥ አርባ ሺህም ፈረ​ሰ​ኞ​ችን ገደለ፤ የሠ​ራ​ዊ​ቱ​ንም አለቃ ሶቤ​ቅን መታ፤ እር​ሱም በዚያ ሞተ።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ለመ​ዋ​ጋት ተሰ​በ​ሰቡ፤ ሠላሳ ሺህ ሰረ​ገ​ሎች፥ ስድ​ስት ሺህም ፈረ​ሰ​ኞች፥ በባ​ሕ​ርም ዳር እን​ዳለ አሸዋ ብዙ ሕዝብ ነበሩ፤ ወጥ​ተ​ውም ከቤ​ቶ​ሮን በአ​ዜብ በኩል በማ​ኪ​ማስ ሰፈሩ።


እን​ስ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንና ድን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን ይዘው በብ​ዛት እንደ አን​በጣ ሆነው ይመ​ጡ​ባ​ቸው ነበር፤ ለእ​ነ​ር​ሱና ለግ​መ​ሎ​ቻ​ቸው ቍጥር አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ያጠ​ፏት ዘንድ ይመጡ ነበር።


ሲሣ​ራም ሰረ​ገ​ሎ​ቹን ሁሉ፥ ዘጠኝ መቶ የብ​ረት ሰረ​ገ​ሎች፥ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝ​ቡን ሁሉ ከአ​ሕ​ዛብ አሪ​ሶት ወደ ቂሶን ወንዝ ሰበ​ሰ​ባ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሶ​ር​ያ​ው​ያን የሰ​ረ​ገላ ድምፅ፥ የፈ​ረስ ድም​ፅና የብዙ ጭፍራ ድምፅ አሰ​ምቶአ​ቸ​ዋ​ልና፥ እርስ በር​ሳ​ቸው “እነሆ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ይከ​ቡን ዘንድ የኬ​ጤ​ዎ​ና​ው​ያ​ን​ንና የግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንን ነገ​ሥት ቀጥሮ አም​ጥ​ቶ​ብ​ናል” ይባ​ባሉ ነበር።


ለአ​ሳም አላ​ባሽ አግሬ ጋሻና ጦር የሚ​ሸ​ከሙ ሦስት መቶ ሺህ የይ​ሁዳ ሠራ​ዊት፥ ወን​ጭፍ የሚ​ወ​ነ​ጭፉ፥ ቀስ​ትም የሚ​ገ​ትሩ ሁለት መቶ ሰማ​ንያ ሺህ የብ​ን​ያም ሰዎች ነበ​ሩት፤ እነ​ዚ​ህም ሁሉ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች ነበሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios