Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 1:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ሰሎ​ሞ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አለው፥ “ከአ​ባቴ ከዳ​ዊት ጋር ታላቅ ምሕ​ረ​ትን አድ​ር​ገ​ሃል፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ አን​ግ​ሠ​ኸ​ኛል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ሰሎሞን እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “ለአባቴ ለዳዊት ታላቅ ቸርነትን አሳይተኸዋል፤ እኔንም በእግሩ ተክተህ አንግሠኸኛል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ሰሎሞንም ጌታን እንዲህ አለው፦ “ለአባቴ ለዳዊት ታላቅና ጽኑ ፍቅር አሳይተኸዋል፥ በእርሱም ፋንታ አንግሠኸኛል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ሰሎሞንም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “አንተ ለአባቴ ለዳዊት ታላቅ ፍቅርህን ባለማቋረጥ አሳይተኸዋል፤ አሁንም እኔ በአባቴ እግር ተተክቼ እንድነግሥ አድርገሃል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ሰሎሞንም እግዚአብሔርን አለው “ከአባቴ ከዳዊት ጋር ታላቅ ምሕረት አድርገሃል፤ በእርሱም ፋንታ አንግሠኸኛል።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 1:8
13 Referencias Cruzadas  

የን​ጉ​ሡን መድ​ኀ​ኒት ታላቅ ያደ​ር​ጋል፤ ቸር​ነ​ቱ​ንም ለቀ​ባው ለዳ​ዊ​ትና ለዘሩ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያደ​ር​ጋል።”


ሰሎ​ሞ​ንም አለ፥ “እርሱ በፊ​ትህ በእ​ው​ነ​ትና በጽ​ድቅ፥ በል​ብም ቅን​ነት ከአ​ንተ ጋር እንደ ሄደ፥ ከአ​ባቴ ከባ​ሪ​ያህ ከዳ​ዊት ጋር ታላቅ ቸር​ነት አድ​ር​ገ​ሃል፤ ዛሬ እንደ ሆነም በዙ​ፋኑ ላይ የሚ​ቀ​መጥ ልጅ ሰጥ​ተህ ታላ​ቁን ቸር​ነ​ት​ህን አቈ​ይ​ተ​ህ​ለ​ታል።


ንጉ​ሡም ዳዊት ገባ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ተቀ​ምጦ እን​ዲህ አለ፥ “አቤቱ አም​ላክ ሆይ፥ ለዘ​ለ​ዓም የወ​ደ​ድ​ኸኝ እኔ ማን ነኝ? ቤቴስ ምን​ድን ነው?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ብዙ ልጆች ሰጥ​ቶ​ኛ​ልና ከል​ጆቼ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ዙፋን ላይ ተቀ​ምጦ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ይነ​ግሥ ዘንድ ልጄን ሰሎ​ሞ​ንን መር​ጦ​ታል።


ሰሎ​ሞ​ንም በአ​ባቱ በዳ​ዊት ዙፋን ላይ ተቀ​መጠ፤ በሁ​ሉም ዘንድ ተወ​ዳጅ ሆነ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ታዘ​ዙ​ለት።


ዕድ​ሜም፥ ባለ​ጠ​ግ​ነ​ትም፥ ክብ​ርም ጠግቦ በመ​ል​ካም ሽም​ግ​ልና ሞተ፤ ልጁም ሰሎ​ሞን በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።


ስሙኝ፤ ጎዳ​ና​ዬን ተከ​ተሉ፤ አድ​ም​ጡ​ኝም፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁም በበ​ረ​ከት ትኖ​ራ​ለች፤ የታ​መ​ነ​ች​ዪ​ቱን የዳ​ዊ​ትን ምሕ​ረት፥ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምን ቃል ኪዳን ከእ​ና​ንተ ጋር አደ​ር​ጋ​ለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos