Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ሳሙኤል 28:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 እርሱ ግን፥ “አል​በ​ላም” ብሎ እንቢ አለ፤ ነገር ግን ብላ​ቴ​ኖ​ቹና ሴቲቱ አስ​ገ​ደ​ዱት፤ ቃላ​ቸ​ው​ንም ሰማ፤ ከም​ድ​ርም ተነ​ሥቶ በአ​ልጋ ላይ ተቀ​መጠ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 እርሱም፣ “አልበላም” በማለት እንቢ አለ። ነገር ግን የራሱ ሰዎች ከሴትየዋ ጋራ ሆነው አጥበቀው ስለ ለመኑት ቃላቸውን ሰማ፤ ከመሬትም ተነሥቶ በዐልጋ ላይ ተቀመጠ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 እርሱም፥ “አልበላም” በማለት እምቢ አለ። ነገር ግን የራሱ ሰዎች ከሴትዮዋ ጋር ሆነው አጥበቀው ስለ ለመኑት ቃላቸውን ሰማ። ከመሬትም ተነሥቶ በአልጋ ላይ ተቀመጠ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ሳኦል “ምንም ነገር አልቀምስም” ብሎ እምቢ አለ፤ ይሁን እንጂ ባለሟሎቹም እንዲመገብ አበረታቱት፤ በመጨረሻም “እሺ” ብሎ ከወደቀበት መሬት በመነሣት አልጋ ላይ ተቀመጠ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 እርሱ ግን፦ አልበላም ብሎ እንቢ አለ፥ ነገር ግን ባሪያዎቹና ሴቲቱ አስገደዱት፥ ቃላቸውንም ሰማ ከምድርም ተነሥቶ በአልጋ ላይ ተቀመጠ።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 28:23
11 Referencias Cruzadas  

ንጉሡ አክ​ዓ​ብም መልሶ፥ “ጌታዬ ሆይ! አንተ እን​ዳ​ልህ፤ እኔ የአ​ንተ ነኝ፤ ለእ​ኔም የሆ​ነው ሁሉ የአ​ንተ ነው” አለ።


የክ​ር​ስ​ቶስ ፍቅር በዚህ አሳብ እን​ድ​ን​ጸና ያስ​ገ​ድ​ደ​ናል፤ ሁሉ ፈጽ​መው ስለ ሞቱ አንዱ ስለ ሁሉ ቤዛ ሆኖ ሞቶ​አ​ልና።


እር​ስ​ዋም ከቤተ ሰቦ​ችዋ ጋር ተጠ​መ​ቀች፤ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አማኝ ካደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ኝስ ወደ ቤቴ ገብ​ታ​ችሁ እደሩ” ብላ ማለ​ደ​ችን፤ የግ​ድም አለ​ችን።


እነ​ር​ሱም፥ “መሽ​ቶ​አ​ልና፥ ፀሐ​ይም ተዘ​ቅ​ዝ​ቆ​አ​ልና፥ ከእኛ ጋር እደር” ብለው ግድ አሉት፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ሊያ​ድር ገባ።


ጌታ​ውም አገ​ል​ጋ​ዩን፦ ወደ መን​ገ​ዶ​ችና ወደ ከተ​ማው ቅጥር ፈጥ​ነህ ሂድና ቤቴ እን​ዲ​መላ ይገቡ ዘንድ ግድ በላ​ቸው አለው።


አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ወደ እርሱ መጥ​ተው፥ “ነቢዩ ታላቅ ነገር ቢነ​ግ​ርህ ባደ​ረ​ግ​ኸው ነበር፤ ይል​ቁ​ንስ፦ ተጠ​መ​ቅና ንጹሕ ሁን ቢልህ እን​ዴት ነዋ!” ብለው ተና​ገ​ሩት።


ከዚ​ህም በኋላ አንድ ቀን እን​ዲህ ሆነ፤ ኤል​ሳዕ ወደ ሱማን አለፈ፤ በዚ​ያም ታላቅ ሴት ነበ​ረች፤ እን​ጀ​ራም ይበላ ዘንድ አቆ​መ​ችው፤ በዚ​ያም ባለፈ ቍጥር እን​ጀራ ሊበላ ወደ​ዚያ ይገባ ነበር።


አሁን እን​ግ​ዲህ አንተ ደግሞ የአ​ገ​ል​ጋ​ይ​ህን ቃል እን​ድ​ት​ሰማ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ በፊ​ት​ህም ቁራሽ እን​ጀራ ላኑ​ር​ልህ፤ መን​ገ​ድም ትሄ​ዳ​ለ​ህና ትበ​ረታ ዘንድ ብላ” አለ​ችው።


በክ​ብር አልጋ ላይ ይቀ​መ​ጣሉ፤ በፊት ለፊ​ታ​ቸ​ውም ማዕድ ተዘ​ጋ​ጅታ ነበር፤ በዕ​ጣ​ኔና በዘ​ይ​ቴም ደስ ይላ​ቸ​ዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios