Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ነገሥት 8:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 በሰ​ማይ ስማ፤ አድ​ር​ግም፤ በባ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ህም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ዳኛ ሁን፤ በበ​ደ​ለ​ኛ​ውም ላይ ፍረድ፤ መን​ገ​ዱ​ንም በራሱ ላይ መል​ስ​በት፤ ጻድ​ቁን አጽ​ድ​ቀው፤ እንደ ጽድ​ቁም ክፈ​ለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ይህን በሰማይ ሆነህ ስማ፤ አድርግም፤ በባሪያዎችህ መካከል ፍረድ፤ ለበደለኛው ስለ አድራጎቱ የእጁን ክፈል፤ ከበደል ነጻ ለሆነውም ንጽሕናውን ይፋ በማድረግ ይህንኑ አረጋግጥለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 በሰማይ ሆነህ ስማ፥ አድርግም፥ ለአገልጋዮችህም ፍርድን ስጥ፤ በበደለኛውም ላይ ፍረድ፤ ስለአካሄዱም ቅጣው፤ ንጹሑንም ነጻ አውጣው፥ እንደ ጽድቁም ክፈለው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 በሰማይ ሆነህ ስማ፤ ለአገልጋዮችህም ፍርድን ስጥ፤ ይኸውም በደል የሠራው ሰው በጥፋቱ መጠን እንዲቀጣ፥ ንጹሑም ነጻ እንዲወጣ አድርግ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 በሰማይ ስማ፤ አድርግም፤ በባሪያዎችህም ላይ ዳኛ ሁን፤ በበደለኛውም ላይ ፍረድ፤ መንገዱንም በራሱ ላይ መልስበት፤ ንጹሑን አጽደቀው፤ እንደ ጽድቁም ክፈለው።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 8:32
22 Referencias Cruzadas  

“በሰ​ዎች መካ​ከል ጠብ ቢሆን፥ ወደ ፍር​ድም ቢመጡ፥ ቢፋ​ረ​ዱም ለጻ​ድቁ ይፈ​ረ​ድ​ለት፤ በበ​ደ​ለ​ኛ​ውም ይፈ​ረ​ድ​በት።


ኀጢ​አ​ትን የም​ት​ሠራ ነፍስ እር​ስዋ ትሞ​ታ​ለች፤ ልጅ የአ​ባ​ቱን ኀጢ​አት አይ​ሸ​ከ​ምም፤ አባ​ትም የል​ጁን ኀጢ​አት አይ​ሸ​ከ​ምም፤ የጻ​ድቁ ጽድቅ በራሱ ላይ ይሆ​ናል፤ የኀ​ጢ​አ​ተ​ኛ​ውም ኀጢ​አት በራሱ ላይ ይሆ​ናል።


በአ​ራጣ ቢያ​በ​ድር፥ አት​ር​ፎም ቢወ​ስድ፥ እን​ደ​ዚህ ያለ ሰው በሕ​ይ​ወት አይ​ኖ​ርም፤ ይህን ርኵ​ሰት ሁሉ አድ​ር​ጎ​አ​ልና ፈጽሞ ይሞ​ታል፤ ደሙም በላዩ ይሆ​ናል።


ለብዙ ሺህ ጽድ​ቅን የሚ​ጠ​ብቅ፥ ቸር​ነ​ትን የሚ​ያ​ደ​ርግ፥ አበ​ሳ​ንና መተ​ላ​ለ​ፍን፥ ኀጢ​አ​ት​ንም ይቅር የሚል፥ በደ​ለ​ኛ​ው​ንም ከቶ የማ​ያ​ነጻ፥ የአ​ባ​ቶ​ች​ንም ኀጢ​አት በል​ጆች፥ እስከ ሦስ​ትና እስከ አራት ትው​ል​ድም በልጅ ልጆች የሚ​ያ​መጣ አም​ላክ ነው” ሲል አወጀ።


እኔም ቀድሞ ኦሪት ሳት​ሠራ ሕያው ነበ​ርሁ፤ የኦ​ሪት ትእ​ዛዝ በመ​ጣች ጊዜ ግን ኀጢ​አት ሕይ​ወ​ትን አገ​ኘች፤ እኔ ግን ሞትሁ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሕግን የሚ​ያ​ደ​ርጉ ይጸ​ድ​ቃሉ እንጂ ሕግን የሚ​ሰሙ አይ​ጸ​ድ​ቁ​ምና።


የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! ስለ​ዚህ እንደ መን​ገዱ በየ​ሰዉ ሁሉ እፈ​ር​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ንስሓ ግቡ፤ ኀጢ​አ​ትም ዕን​ቅ​ፋት እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ባ​ችሁ ከኀ​ጢ​አ​ታ​ችሁ ሁሉ ተመ​ለሱ።


ኃጥኡን ጻድቅ፥ ጻድቁንም ኃጥእ ብሎ መፍረድ በእግዚአብሔር ዘንድ የረከሰና የተናቀ ነው።


ስለዚህ የሥራቸውን ፍሬ ይበላሉ፥ በራሳቸውም ኀጢአት ይጠግባሉ።


ውኃ​ውን ካጠ​ጣት በኋላ እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ ራስ​ዋን አር​ክ​ሳና ባል​ዋን ቸል ብላው ከሆነ፤ የመ​ር​ገሙ መራራ ውኃ ወደ ሆድዋ ይገ​ባል፤ ሆድ​ዋ​ንም ይሰ​ነ​ጥ​ቀ​ዋል፤ ጎኗም ይረ​ግ​ፋል፤ ሴቲ​ቱም በሕ​ዝ​ብዋ መካ​ከል ለመ​ር​ገም ትሆ​ና​ለች።


ከዐ​መፅ ፍርድ ሁሉ ራቅ፤ በደል የሌ​ለ​በ​ት​ንና ጻድ​ቅን አት​ግ​ደል፤ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ው​ንም በመ​ማ​ለጃ አታ​ድን፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ጽድቄ ይከ​ፍ​ለ​ኛል፤ እንደ እጄ ንጽ​ሕ​ናም ይመ​ል​ስ​ል​ኛል፤


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ዘር ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ድ​ቃሉ፤ ይከ​ብ​ራ​ሉም ይባ​ላል።


ሰውስ ሰውን ቢበ​ድል ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ል​ዩ​ለ​ታል፤ ሰው ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቢበ​ድል ስለ እርሱ ወደ ማን ይጸ​ል​ዩ​ለ​ታል?” እነ​ርሱ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ጠ​ፋ​ቸው ወድ​ዶ​አ​ልና የአ​ባ​ታ​ቸ​ውን ቃል አል​ሰ​ሙም።


አባቴ ዳዊት ሳያ​ውቅ ከእ​ርሱ የሚ​ሻ​ሉ​ትን ሁለ​ቱን ጻድ​ቃን ሰዎች፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሠራ​ዊት አለቃ የኔ​ርን ልጅ አበ​ኔ​ርን፥ የይ​ሁ​ዳ​ንም ሠራ​ዊት አለቃ የኢ​ያ​ቴ​ርን ልጅ አሜ​ሳ​ይን በሰ​ይፍ ገድ​ሎ​አ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዐ​መፅ ደሙን በራሱ ላይ መለሰ።


ደማ​ቸ​ውም በኢ​ዮ​አብ ራስና በዘሩ ራስ ላይ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይመ​ለስ፤ ለዳ​ዊት ግን ለዘ​ሩና ለቤቱ፥ ለዙ​ፋ​ኑም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰላም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይሁን።”


የኃ​ጥ​ኣን ክፋት ያል​ቃል፥ ጻድ​ቃ​ንን ግን ታቃ​ና​ቸ​ዋ​ለህ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልቡ​ና​ንና ኵላ​ሊ​ትን ይመ​ረ​ም​ራል።


“እኔም ደግሞ በዐ​ይኔ አል​ራ​ራም፤ ይቅ​ር​ታም አላ​ደ​ር​ግም፤ መን​ገ​ዳ​ቸ​ው​ንም በራ​ሳ​ቸው ላይ እመ​ል​ሳ​ለሁ” አለኝ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios