Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 6:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ሁለ​ቱም ኪሩ​ቤል በው​ስ​ጠ​ኛው ቤት መካ​ከል ነበሩ። የኪ​ሩ​ቤ​ልም ክን​ፎ​ቻ​ቸው ተዘ​ር​ግ​ተው ነበር፤ የአ​ን​ዱም ኪሩብ ክንፍ አን​ደ​ኛ​ውን ግንብ ይነካ ነበር፤ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ኪሩብ ክንፍ ሁለ​ተ​ኛ​ውን ግንብ ይነካ ነበር፤ የሁ​ለ​ቱም ክን​ፎች በቤቱ መካ​ከል እርስ በር​ሳ​ቸው ይነ​ካኩ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ክንፎቻቸው እንደ ተዘረጋ፣ ኪሩቤልን ወስዶ በቅድስተ ቅዱሳኑ አኖራቸው፤ የአንዱ ኪሩብ ክንፍ አንዱን ግድግዳ ሲነካ፣ የሌላው ኪሩብ ክንፍ ደግሞ ሌላውን ግድግዳ ይነካ ነበር፤ ሌሎቹ ክንፎቻቸውም በቅድስተ ቅዱሳኑ መካከል እርስ በርሳቸው ይነካኩ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ኪሩቤልንም በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ እንዲቆሙ አደረገ፤ ስለዚህም የተዘረጉ ሁለቱ ክንፎቻቸው በክፍሉ መካከለኛ ቦታ ላይ ተገናኝተው ሌሎቹ ሁለቱ ክንፎቻቸው ደግሞ በተዘረጉበት አቅጣጫ ግንቦቹን ይነኩ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ኪሩቤልንም በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ እንዲቆሙ አደረገ፤ ስለዚህም የተዘረጉ ሁለቱ ክንፎቻቸው በክፍሉ መካከለኛ ቦታ ላይ ተገናኝተው ሌሎቹ ሁለቱ ክንፎቻቸው ደግሞ በተዘረጉበት አቅጣጫ ግንቦቹን ይነኩ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ኪሩቤልንም በውስጠኛው ቤት አኖራቸው፤ የኪሩቤልም ክንፎቻቸው ተዘርግተው ነበር፤ የአንዱም ኪሩብ ክንፍ አንደኛውን ግንብ ይነካ ነበር፤ የሁለተኛውም ኪሩብ ክንፍ ሁለተኛውን ግንብ ይነካ ነበር፤ የሁለቱም ክንፎች በቤቱ መካከል እርስ በርሳቸው ይነካኩ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 6:27
8 Referencias Cruzadas  

የአ​ንዱ ኪሩብ ቁመት ዐሥር ክንድ ነበረ፤ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ኪሩብ እን​ዲሁ ነበረ።


ኪሩ​ቤ​ል​ንም በወ​ርቅ ለበ​ጣ​ቸው።


ካህ​ና​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ታቦት በቤቱ በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳን ውስጥ ከኪ​ሩ​ቤል ክንፍ በታች ወደ ነበ​ረው ወደ ስፍ​ራዋ አገቧት።


ኪሩ​ቤ​ልም በታ​ቦቷ ስፍራ ላይ ክን​ፎ​ቻ​ቸ​ውን ዘር​ግ​ተው ነበር፤ ኪሩ​ቤ​ልም ታቦቷ​ንና የተ​ቀ​ደሱ ዕቃ​ዎ​ችን በስ​ተ​ላይ በኩል ሸፍ​ነው ነበር።


የኪ​ሩ​ቤ​ልም ክን​ፎች ሃያ ክንድ ሙሉ ተዘ​ር​ግ​ተው ነበር፤ የአ​ንዱ የኪ​ሩብ ክንፍ ርዝ​መት አም​ስት ክንድ ነበረ፤ የቤ​ቱ​ንም ግንብ ይነካ ነበር፤ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ክንፍ ርዝ​መት አም​ስት ክንድ ነበረ፤ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ው​ንም ኪሩብ ክንፍ ይነካ ነበር።


ኪሩ​ቤ​ልም በታ​ቦቷ ስፍራ ላይ ክን​ፎ​ቻ​ቸ​ውን ዘር​ግ​ተው ነበር፤ ኪሩ​ቤ​ልም ታቦ​ቷ​ንና መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹን በስ​ተ​ላዩ በኩል ይሸ​ፍኑ ነበር።


ኪሩ​ቤ​ልም ክን​ፎ​ቻ​ቸ​ውን ወደ ላይ ይዘ​ረ​ጋሉ፤ የስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ው​ንም በክ​ን​ፎ​ቻ​ቸው ይሸ​ፍ​ናሉ፤ ፊታ​ቸ​ውም እርስ በርሱ ይተ​ያ​ያል፤ የኪ​ሩ​ቤ​ልም ፊቶ​ቻ​ቸው ወደ ስር​የት መክ​ደ​ኛው ይሁን።


ኪሩ​ቤ​ልም ክን​ፎ​ቻ​ቸ​ውን ወደ ላይ የዘ​ረጉ ሆኑ፥ የስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ው​ንም በክ​ን​ፎ​ቻ​ቸው ሸፈኑ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ተያዩ፤ የኪ​ሩ​ቤ​ልም ፊቶ​ቻ​ቸው ወደ መክ​ደ​ኛው ተመ​ለ​ከቱ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos