Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 20:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ሚስቱ ኤል​ዛ​ቤ​ልም፥ “አሁ​ንም አንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ሆነህ እን​ደ​ዚህ ታደ​ር​ጋ​ለ​ህን? ተነሣ፤ እን​ጀ​ራ​ንም ብላ፤ ራስ​ህ​ንም አጽና፤ ልብ​ህም ደስ ይበ​ላት፤ የኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊ​ው​ንም የና​ቡ​ቴን የወ​ይን ቦታ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ” አለ​ችው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 የእስራኤልም ንጉሥ የአገሩን ሽማግሌዎች ሁሉ ጠርቶ፣ “ይህ ሰው እንዴት ጠብ እንደሚፈልግ ታያላችሁ፤ ሚስቶቼንና ልጆቼን፣ ብሬንና ወርቄን እንዳስረክበው በጠየቀኝ ጊዜ አልከለከልሁትም” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ንጉሥ አክዓብም የሀገሪቱን ሽማግሌዎች ሁሉ ጠርቶ “ይህ ሰው ምን ዓይነት ጠብ እንደሚፈልግ ተመልከቱ። ከዚህ በፊት ሚስቶቼንና ልጆቼን፥ ብሬንና ወርቄን እንዳስረክበው ጠይቆኝ ተስማምቼ ነበር” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ንጉሥ አክዓብም የሀገሪቱን ሽማግሌዎች ሁሉ ጠርቶ “ይህ ሰው ምን ዐይነት ጠብ እንደሚፈልግ ተመልከቱ። ከዚህ በፊት ሚስቶቼንና ልጆቼን፥ ብሬንና ወርቄን እንዳስረክበው ጠይቆኝ ተስማምቼ ነበር” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ሚስቱም ኤልዛቤል “አንተ አሁን የእስራኤልን መንግሥት ትገዛለህን? ተነሣ፤ እንጀራም ብላ፤ ልብህም ደስ ይበላት፤ የኢይዝራኤላዊውን የናቡቴን የወይን ቦታ እሰጥሃለሁ፤” አለችው።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 20:7
18 Referencias Cruzadas  

እር​ሱም፥ “ኢይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊ​ውን ናቡ​ቴን፦ የወ​ይ​ን​ህን ቦታ በገ​ን​ዘብ ስጠኝ፤ ወይም ብት​ወ​ድድ በፋ​ን​ታው ሌላ የወ​ይን ቦታ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ ብዬ ተና​ገ​ር​ሁት፤ እርሱ ግን የአ​ባ​ቶ​ቼን ርስት አል​ሰ​ጥ​ህም ስለ አለኝ ነው” አላት።


በአ​ክ​ዓ​ብም ስም ደብ​ዳቤ ጻፈች፤ በማ​ኅ​ተ​ሙም አተ​መ​ችው፤ በከ​ተ​ማው ወደ ነበ​ሩ​ትና ከና​ቡ​ቴም ጋር ወደ ተቀ​መ​ጡት ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና አለ​ቆች ደብ​ዳ​ቤ​ውን ላከች።


አለ​ቆ​ችና ሕዝ​ቡም ሁሉ፥ “እንቢ በለው፤ እሺም አት​በ​ለው” አሉት።


ሰሎ​ሞ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤትና የራ​ሱን ቤተ መን​ግ​ሥት ሠርቶ ከፈ​ጸመ ከሃያ ዓመት በኋላ ያን​ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ታቦት ከዳ​ዊት ከተማ ከጽ​ዮን ያወጡ ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና የነ​ገድ አለ​ቆ​ችን ሁሉ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ቤቶች መሳ​ፍ​ንት ንጉሡ ሰሎ​ሞን በጽ​ዮን ሰበ​ሰ​ባ​ቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ደብ​ዳ​ቤ​ውን ባነ​በበ ጊዜ ልብ​ሱን ቀድዶ፥ “ሰውን ከለ​ምጹ እፈ​ውስ ዘንድ ይህ ሰው ወደ እኔ መስ​ደዱ እኔ በውኑ ለመ​ግ​ደ​ልና ለማ​ዳን የም​ችል አም​ላክ ነኝን? ተመ​ል​ከቱ፥ የጠብ ምክ​ን​ያት እን​ደ​ሚ​ፈ​ል​ግ​ብኝ ተመ​ል​ከቱ” አለ።


ዳዊ​ትም ከሻ​ለ​ቆ​ችና ከመቶ አለ​ቆች፥ ከአ​ለ​ቆ​ቹም ሁሉ ጋር ተማ​ከረ።


ዳዊ​ትም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አለ​ቆች ሁሉና የፍ​ርድ አለ​ቆ​ችን፥ ንጉ​ሡ​ንም በየ​ተራ የሚ​ጠ​ብ​ቁ​ትን አለ​ቆ​ቹን፥ ሻለ​ቆ​ቹ​ንም፥ የመቶ አለ​ቆ​ቹ​ንም፥ በን​ጉ​ሡና በል​ጆቹ ሀብ​ትና ንብ​ረት ላይ፥ መባ ባለ​በት ላይ የተ​ሾ​ሙ​ትን ጃን​ደ​ረ​ቦ​ች​ንም፥ ኀያ​ላ​ኑ​ንና ሰል​ፈ​ኞ​ቹን ሁሉ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሰበ​ሰበ።


በሆ​ዳ​ቸው ጭን​ቅ​ትን ይፀ​ን​ሳሉ፥ ከንቱ ነገ​ር​ንም ይወ​ል​ዳሉ። ሆዳ​ቸ​ውም ተን​ኰ​ልን ያዘ​ጋ​ጃል።”


ጸሎ​ቴን በፊ​ትህ እንደ ዕጣን ተቀ​በ​ል​ልኝ፥ እጆቼ የሠ​ርክ መሥ​ዋ​ዕ​ትን አነሡ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይበ​ልህ፥ የል​ብ​ህ​ንም መሻት ይሰ​ጥ​ሃል።


ምሕ​ረ​ትህ ከሕ​ይ​ወት ይሻ​ላ​ልና፥ ከን​ፈ​ሮቼ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል።


እነሆ፥ ዐመ​ፀኛ በዐ​መፁ ተጨ​ነቀ፤ ጭን​ቅን ፀነሰ፤ ኀጢ​አ​ት​ንም ወለደ።


መምህር የሌላቸው እንደ ቅጠል ይወድቃሉ። በምክር ብዛት ግን ደኅንነት ይኖራል።


መልካምን የሚያስብ መልካም ክብርን ይወድዳል። ክፋትን የሚፈልግን ግን ክፋት ታገኘዋለች።


ልባቸው ሐሰትን ይማራልና። ከንፈራቸውም ምቀኝነትን ይናገራልና።


ጠማማ ልቡ ሁልጊዜ ክፋትን ያስባል፤ እንደዚህም ያለ ሰው ጠብን በከተማ ላይ ይዘራል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos