Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ነገሥት 12:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ሮብ​ዓም ግን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጣ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ቤት ወግ​ተው መን​ግ​ሥ​ቱን ወደ ሰሎ​ሞን ልጅ ወደ ሮብ​ዓም ይመ​ልሱ ዘንድ ከይ​ሁዳ ቤት ሁሉና ከብ​ን​ያም ነገድ የተ​መ​ረ​ጡ​ትን አንድ መቶ ሃያ ሺህ ተዋ​ጊ​ዎች ሰዎ​ችን ሰበ​ሰበ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ሮብዓም ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ፣ የእስራኤልን ቤት ወግተው መንግሥቱን ለሰሎሞን ልጅ ለሮብዓም እንዲመልሱ መላውን የይሁዳ ቤትና የብንያምን ነገድ ሰበሰበ፤ የሰራዊቱም ቍጥር አንድ መቶ ሰማንያ ሺሕ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ሮብዓም ወደ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከይሁዳና ከብንያም ነገዶች ተውጣጥተው የተመለሱ አንድ መቶ ሰማኒያ ሺህ ምርጥ ወታደሮች ጠርቶ በአንድነት ሰበሰበ፤ ይህንንም ያደረገው የእስራኤልን ነገዶች ወግቶ ግዛቱን እንደገና በቁጥጥሩ ሥር ለማድረግ ዐቅዶ ስለ ነበር ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ሮብዓም ወደ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከይሁዳና ከብንያም ነገዶች ተውጣጥተው የተመለሱ አንድ መቶ ሰማኒያ ሺህ ምርጥ ወታደሮች ጠርቶ በአንድነት ሰበሰበ፤ ይህንንም ያደረገው የእስራኤልን ነገዶች ወግቶ ግዛቱን እንደገና በቊጥጥሩ ሥር ለማድረግ ዐቅዶ ስለ ነበር ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ሮብዓምም ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፤ የእስራኤልንም ቤት ወግተው መንግሥቱን ወደ ሰሎሞን ልጅ ወደ ሮብዓም ይመልሱ ዘንድ ከይሁዳ ቤት ሁሉና ከብንያም ነገድ የተመረጡትን አንድ መቶ ሰማንያ ሺህ ሰልፈኞች ሰዎች ሰበሰበ።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 12:21
8 Referencias Cruzadas  

አሳም፥ “አቤቱ፥ በብ​ዙም ሆነ በጥ​ቂቱ ማዳን አይ​ሳ​ን​ህም፤ አቤቱ፥ አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ በአ​ንተ ታም​ነ​ና​ልና፥ በስ​ም​ህም በዚህ ታላቅ ወገን ላይ መጥ​ተ​ና​ልና ርዳን፤ አቤቱ፥ አም​ላ​ካ​ችን አንተ ነህ፤ ሰውም አያ​ሸ​ን​ፍ​ህም” ብሎ ወደ አም​ላኩ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ።


ለአ​ሳም አላ​ባሽ አግሬ ጋሻና ጦር የሚ​ሸ​ከሙ ሦስት መቶ ሺህ የይ​ሁዳ ሠራ​ዊት፥ ወን​ጭፍ የሚ​ወ​ነ​ጭፉ፥ ቀስ​ትም የሚ​ገ​ትሩ ሁለት መቶ ሰማ​ንያ ሺህ የብ​ን​ያም ሰዎች ነበ​ሩት፤ እነ​ዚ​ህም ሁሉ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች ነበሩ።


ኢዮ​አ​ብም የቈ​ጠ​ራ​ቸ​ውን የሕ​ዝ​ቡን ድምር ለዳ​ዊት ሰጠ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ አንድ ሚሊ​ዮን አንድ መቶ ሺህ ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ ሰዎች ተገኙ፤ ከይ​ሁ​ዳም አራት መቶ ሰባ ሺህ ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ ሰዎች ተገኙ።


ስለ ባሪ​ያዬ ስለ ዳዊት ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሀገ​ሮች ሁሉ ስለ መረ​ጥ​ኋት ከተማ ስለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ግን ሁለት ነገድ ይቀ​ሩ​ለ​ታል፤


በዘ​መ​ኑም ሁሉ በሮ​ብ​ዓ​ምና በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም መካ​ከል ጦር​ነት ነበረ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios