Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 11:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ም​ንም አለው፥ “ዐሥር ቅዳጅ ውሰድ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ እነሆ፥ ከሰ​ሎ​ሞን እጅ መን​ግ​ሥ​ቱን እለ​ያ​ታ​ለሁ፤ ዐሥ​ሩ​ንም ነገ​ዶች እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ከዚያም ኢዮርብዓምን እንዲህ አለው፤ “ዐሥሩን ቍራጭ ለራስህ ውሰድ፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ‘እነሆ፤ መንግሥቱን ከሰሎሞን እጅ እቀድዳለሁ፤ ዐሥሩን ነገድ ለአንተ እሰጣለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ኢዮርብዓምንም እንዲህ አለው፤ “ዐሥሩን ቁራጭ ለራስህ ውሰድ፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ ‘መንግሥትን ከሰሎሞን ወስጄ ዐሥሩን ነገድ ለአንተ እሰጥሃለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ኢዮርብዓምንም እንዲህ አለው፤ “ዐሥሩን ቊራጭ ለራስህ ውሰድ፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ ‘መንግሥትን ከሰሎሞን ወስጄ ዐሥሩን ነገድ ለአንተ እሰጥሃለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ኢዮርብዓምንም አለው “ዐሥር ቁራጭ ውሰድ፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና ‘እነሆ፥ ከሰሎሞን እጅ መንግሥቱን እቀድዳለሁ፤ ዐሥሩንም ነገዶች እሰጥሃለሁ፤

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 11:31
9 Referencias Cruzadas  

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ለይ​ሁዳ ሰዎች መል​ሰው፥ “በን​ጉሡ ዘንድ ለእኛ ዐሥር ክፍል አለን፤ ከእ​ና​ን​ተም እኛ እን​ቀ​ድ​ማ​ለን፤ እኛም በኵር ነን፤ ለዳ​ዊ​ትም ከእ​ና​ንተ እኛ እን​ቀ​ር​ባ​ለን፤ ስለ​ምን ናቃ​ች​ሁን? ንጉ​ሡ​ንስ እን​መ​ል​ሰው ዘንድ ከእ​ና​ንተ የእኛ ቃል አይ​ቀ​ድ​ም​ምን?” አሏ​ቸው። የይ​ሁ​ዳም ሰዎች ቃል ከእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ቃል ይልቅ ጠነ​ከረ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሴ​ሎ​ና​ዊው በአ​ኪያ አፍ ለና​ባጥ ልጅ ለኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም የተ​ና​ገ​ረ​ውን ነገር እን​ዲ​ያ​ጸና ለውጡ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነበ​ርና ንጉሡ ሕዝ​ቡን አል​ሰ​ማም።


ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ሚስቱ ሐኖ​ንን፥ “ተነሺ፥ ራስ​ሽን ለውጪ የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ሚስት እንደ ሆንሽ ማንም አይ​ወቅ፤ ወደ ሴሎም ሂጂ፤ ስለ​ዚ​ህም ሕፃን ከደ​ዌው ይድን እን​ደ​ሆነ ጠይቂ፤ እነሆ፥ በዚህ ሕዝብ ላይ እን​ደ​ም​ነ​ግሥ የነ​ገ​ረኝ ነቢዩ አኪያ በዚያ አለ።


ከዳ​ዊ​ትም ቤት፤ መን​ግ​ሥ​ቱን ከፍዬ ሰጥ​ቼህ ነበር፤ ነገር ግን በፍ​ጹም ልቡ እንደ ተከ​ተ​ለኝ፥ በፊ​ቴም ቅን ነገር ብቻ እን​ዳ​ደ​ረገ፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም እንደ ጠበቀ እንደ ባሪ​ያዬ እንደ ዳዊት አል​ሆ​ን​ህም።


እስ​ራ​ኤ​ልም ከዳ​ዊት ቤት ተለዩ፤ የና​ባ​ጥ​ንም ልጅ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምን አነ​ገሡ፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከመ​ከ​ተል እስ​ራ​ኤ​ልን መለሰ፤ ታላ​ቅም ኀጢ​አት አሠ​ራ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሴ​ሎ​ና​ዊው በአ​ኪያ ቃል ስለ ናባጥ ልጅ ስለ ኢዮ​ር​ብ​ዓም የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃሉን እን​ዲ​ያ​ጸና ለውጡ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነበ​ርና ንጉሡ ሕዝ​ቡን አል​ሰ​ማም።


ሳሙ​ኤ​ልም ሊሄድ ዘወር ባለ ጊዜ ሳኦል የል​ብ​ሱን ጫፍ ያዘ፤ ተቀ​ደ​ደም።


ሳሙ​ኤ​ልም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል መን​ግ​ሥ​ት​ህን ዛሬ ከእ​ጅህ ቀደ​ዳት፤ ከአ​ን​ተም ለሚ​ሻል ለባ​ል​ን​ጀ​ራህ አሳ​ልፎ ሰጣት፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos