Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ነገሥት 11:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ከዚህ በኋ​ላም ኢዮ​ር​ብ​ዓም ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በወጣ ጊዜ ሴሎ​ና​ዊው ነቢዩ አኪያ በመ​ን​ገድ ላይ ተገ​ና​ኘው፤ ከመ​ን​ገ​ድም ገለል አደ​ረ​ገው፤ አኪ​ያም አዲስ ልብስ ለብሶ ነበር። ሁለ​ቱም በሜዳ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 በዚያ ጊዜም ኢዮርብዓም ከኢየሩሳሌም ሲወጣ፣ የሴሎው ነቢይ አኪያ በመንገድ ላይ ተገናኘው፤ አኪያም አዲስ መጐናጸፊያ ለብሶ ነበር፤ ሁለቱ ብቻቸውን ሳሉ፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 አንድ ቀን ኢዮርብዓም ከኢየሩሳሌም ወጥቶ በጉዞ ላይ ሳለ አዲስ መጐናጸፊያ የለበሰ፥ ከሴሎ የመጣው ነቢዩ አኪያ ከከተማ ውጪ መንገድ ላይ ብቻውን አገኘው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 አንድ ቀን ኢዮርብዓም ከኢየሩሳሌም ወጥቶ በጒዞ ላይ ሳለ አዲስ መጐናጸፊያ የለበሰ፥ ከሴሎ የመጣው ነቢዩ አኪያ ከከተማ ውጪ መንገድ ላይ ብቻውን አገኘው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 በዚያን ጊዜም ኢዮርብዓም ከኢየሩሳሌም በወጣ ጊዜ ሴሎናዊው ነቢዩ አኪያ በመንገድ ላይ ተገናኘው፤ አኪያም አዲስ ልብስ ለብሶ ነበር፤ ሁለቱም በሜዳው ለብቻቸው ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 11:29
10 Referencias Cruzadas  

የቀ​ረ​ውም ፊተ​ኛ​ውና ኋለ​ኛው የሰ​ሎ​ሞን ነገር በነ​ቢዩ በና​ታን ታሪክ፥ በሴ​ሎ​ና​ዊ​ውም በአ​ኪያ ትን​ቢት፥ ስለ ናባ​ጥም ልጅ ስለ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ባየው በባለ ራእዩ በኢ​ዩ​ሔል ራእይ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ሚስቱ ሐኖ​ንን፥ “ተነሺ፥ ራስ​ሽን ለውጪ የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ሚስት እንደ ሆንሽ ማንም አይ​ወቅ፤ ወደ ሴሎም ሂጂ፤ ስለ​ዚ​ህም ሕፃን ከደ​ዌው ይድን እን​ደ​ሆነ ጠይቂ፤ እነሆ፥ በዚህ ሕዝብ ላይ እን​ደ​ም​ነ​ግሥ የነ​ገ​ረኝ ነቢዩ አኪያ በዚያ አለ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሴ​ሎ​ና​ዊው በአ​ኪያ አፍ ለና​ባጥ ልጅ ለኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም የተ​ና​ገ​ረ​ውን ነገር እን​ዲ​ያ​ጸና ለውጡ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነበ​ርና ንጉሡ ሕዝ​ቡን አል​ሰ​ማም።


ለእ​ኔም ለአ​ገ​ል​ጋ​ይህ ሁለት ወን​ዶች ልጆች ነበ​ሩኝ፤ በሜ​ዳም ተጣሉ፤ የሚ​ገ​ላ​ግ​ላ​ቸ​ውም አል​ነ​በ​ረም፤ አን​ዱም ሌላ​ውን መትቶ ገደ​ለው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በሴሎ ተሰ​በ​ሰቡ፤ በዚ​ያም የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ተከሉ፤ ምድ​ሩም ጸጥ ብሎ ተገ​ዛ​ላ​ቸው።


ቃየ​ልም ወን​ድ​ሙን አቤ​ልን፥ “ና ወደ ሜዳ እን​ሂድ” አለው። በሜ​ዳም ሳሉ ቃየል በወ​ን​ድሙ በአ​ቤል ላይ ተነ​ሣ​በት፤ ገደ​ለ​ውም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰሎ​ሞ​ንን አለው፥ “ይህን ሠር​ተ​ሃ​ልና፥ ያዘ​ዝ​ሁ​ህ​ንም ትእ​ዛ​ዜ​ንና ሕጌን አል​ጠ​ብ​ቅ​ህ​ምና መን​ግ​ሥ​ት​ህን ከአ​ንተ ከፍዬ ለባ​ሪ​ያህ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ።


የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ሚስት እን​ዲሁ አደ​ረ​ገች፤ ተነ​ሥ​ታም እን​ጀራ፥ የወ​ይን ዘለ​ላና አንድ ማሠሮ ማር በመ​ያዝ ወደ ሴሎ ሄደች፤ ወደ አኪ​ያም ቤት ገባች። አኪያ ግን ስለ መሸ​ም​ገሉ ዐይ​ኖቹ ፈዝ​ዘው ነበ​ርና ማየት አል​ቻ​ለም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሴ​ሎ​ና​ዊው በአ​ኪያ ቃል ስለ ናባጥ ልጅ ስለ ኢዮ​ር​ብ​ዓም የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃሉን እን​ዲ​ያ​ጸና ለውጡ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነበ​ርና ንጉሡ ሕዝ​ቡን አል​ሰ​ማም።


እን​ዲ​ህም ሆነ፥ የና​ባጥ ልጅ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ገና በግ​ብፅ ሳለ ይህን በሰማ ጊዜ፥ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ከን​ጉሡ ከሰ​ሎ​ሞን ፊት ኰብ​ልሎ በግ​ብፅ ተቀ​ምጦ ነበረ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios