Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ነገሥት 1:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ሄደሽ ወደ ንጉሡ ወደ ዳዊት ግቢና፦ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ለእኔ ለአ​ገ​ል​ጋ​ይህ፦ ልጅሽ ሰሎ​ሞን ከእኔ በኋላ ይነ​ግ​ሣል፤ በዙ​ፋ​ኔም ይቀ​መ​ጣል ብለህ አል​ማ​ል​ህ​ል​ኝ​ምን? ስለ​ም​ንስ አዶ​ን​ያስ ይነ​ግ​ሣል? በዪው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ወደ ንጉሥ ዳዊት ሂጂና፣ ‘ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ “ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ ቀጥሎ ይነግሣል፤ በዙፋኔም ይቀመጣል” ብለህ ለእኔ ለአገልጋይህ አልማልህልኝም ነበር? ታዲያ አዶንያስ የነገሠው ስለ ምንድን ነው?’ በዪው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ሄደሽ ወደ ንጉሡ ወደ ዳዊት ግቢና፦ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ለእኔ ለባርያህ፦ ‘ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፥ በዙፋኔም ይቀመጣል’ ብለህ አልማልህልኝምን? ስለ ምንስ አዶንያስ ይነግሣል? በዪው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ወደ ንጉሥ ዳዊት ገብተሽ ‘ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ነግሦ በዙፋኔ ይቀመጣል’ ብለህ ለአገልጋይህ በመሐላ ቃል ገብተህልኝ አልነበረምን? ታዲያ፥ አሁን አዶንያስ እንዴት ሊነግሥ ቻለ? ብለሽ ንገሪው”።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ሄደሽ ወደ ንጉሡ ወደ ዳዊት ግቢና ‘ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! ለእኔ ለባሪያህ ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፤ በዙፋኔም ይቀመጣል፤ ብለህ አልማልህልኝምን? ስለ ምንስ አዶንያስ ይነግሣል?’ በዪው።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 1:13
16 Referencias Cruzadas  

በእ​ው​ነት፦ ልጅሽ ሰሎ​ሞን ከእኔ በኋላ ይነ​ግ​ሣል፤ በእ​ኔም ፋንታ በዙ​ፋኔ ላይ ይቀ​መ​ጣል ብዬ በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ማል​ሁ​ልሽ፥ እን​ዲሁ ዛሬ በእ​ው​ነት አደ​ር​ጋ​ለሁ።”


እር​ስ​ዋም አለ​ችው፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ አንተ ለአ​ገ​ል​ጋ​ይህ፦ ልጅሽ ሰሎ​ሞን ከእኔ በኋላ ይነ​ግ​ሣል፤ በዙ​ፋ​ኔም ይቀ​መ​ጣል ብለህ በአ​ም​ላ​ክህ ምለ​ህ​ልኝ አል​ነ​በ​ረ​ምን?


በዙ​ፋኑ ላይ የሚ​ነ​ግሥ ልጅ እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ለት ከባ​ሪ​ያዬ ከዳ​ዊት ጋር፥ ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችም ከሌ​ዋ​ው​ያን ካህ​ናት ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ደግሞ ይፈ​ር​ሳል።


ለአ​ለ​ቆች ሰላ​ምን ለእ​ር​ሱም ሕይ​ወ​ትን አመ​ጣ​ለ​ሁና፤ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ በፍ​ር​ድና በጽ​ድቅ ያጸ​ና​ውና ይደ​ግ​ፈው ዘንድ ግዛቱ ታላቅ ይሆ​ናል፤ በዳ​ዊት ዙፋን መን​ግ​ሥቱ ትጸ​ና​ለች፤ ለሰ​ላ​ሙም ፍጻሜ የለ​ውም። የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅን​ዐት ይህን ያደ​ር​ጋል።


ሰሎ​ሞ​ንም በአ​ባቱ በዳ​ዊት ዙፋን ላይ ተቀ​መጠ፤ በሁ​ሉም ዘንድ ተወ​ዳጅ ሆነ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ታዘ​ዙ​ለት።


ሰሎ​ሞ​ንም በአ​ባቱ በዳ​ዊት ዙፋን ተቀ​መጠ፤ መን​ግ​ሥ​ቱም እጅግ ጸና።


ንጉ​ሡም፥ “ዐይኔ እያየ ዛሬ በዙ​ፋኔ ላይ የሚ​ቀ​መ​ጠ​ውን ዘር የሰ​ጠኝ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን” አለ።


ነቢዩ ናታ​ንም አለ፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፦ አንተ ከእኔ በኋላ አዶ​ን​ያስ ይነ​ግ​ሣል፥ በዙ​ፋኔ ላይም ይቀ​መ​ጣል ብለ​ሃ​ልን?


ናታ​ንም የሰ​ሎ​ሞ​ንን እናት ቤር​ሳ​ቤ​ህን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራት፥ “ጌታ​ችን ዳዊት ሳያ​ውቅ የአ​ጊት ልጅ አዶ​ን​ያስ እንደ ነገሠ አል​ሰ​ማ​ሽ​ምን?


በኋ​ላ​ውም ተከ​ት​ላ​ችሁ ውጡ፤ እር​ሱም መጥቶ በዙ​ፋኔ ላይ ይቀ​መጥ፤ በእ​ኔም ፋንታ ይን​ገሥ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁ​ዳም ላይ ይነ​ግሥ ዘንድ አዝ​ዣ​ለሁ።”


“በግ​ዛ​ቱም በተ​ቀ​መጠ ጊዜ ከሌ​ዋ​ው​ያን ካህ​ናት ወስዶ ይህን ሁለ​ተኛ ሕግ ለራሱ በመ​ጽ​ሐፍ ይጻፍ።


እነሆ፥ አንቺ በዚያ ለን​ጉሥ ስት​ነ​ግሪ እኔ ከአ​ንቺ በኋላ እገ​ባ​ለሁ፤ ቃል​ሽ​ንም አጸ​ና​ለሁ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ብዙ ልጆች ሰጥ​ቶ​ኛ​ልና ከል​ጆቼ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ዙፋን ላይ ተቀ​ምጦ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ይነ​ግሥ ዘንድ ልጄን ሰሎ​ሞ​ንን መር​ጦ​ታል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios