Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 8:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ችሁ ላይ እን​ዲህ የም​ት​በ​ድሉ ከሆነ ደካማ ሕሊ​ና​ቸ​ው​ንም የም​ታ​ቈ​ስሉ ከሆነ ክር​ስ​ቶ​ስን ትበ​ድ​ላ​ላ​ችሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 በዚህ መንገድ ወንድሞቻችሁን በመበደልና ደካማ ኅሊናቸውን በማቍሰል፣ ክርስቶስን ትበድላላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እንግዲህ ወንድሞችን እየበደላችሁ ደካማም የሆነውን ሕሊናቸውን እያቆሰላችሁ ክርስቶስን ትበድላላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በዚሁ ሁኔታ ክርስቲያን ወንድሞቻችሁን በመበደልና ደካማ ኅሊናቸውንም በማቊሰል ክርስቶስን ትበድላላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እንዲህም ወንድሞችን እየበደላችሁ ደካማም የሆነውን ሕሊናቸውን እያቆሰላችሁ ክርስቶስን ትበድላላችሁ።

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 8:12
18 Referencias Cruzadas  

በእኔም ከሚያምኑ ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ፥ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር መስጠም ይሻለው ነበር።


ያን ጊዜ ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም፤’ ብሎ ይመልስላቸዋል።


አካል አንድ እንደ ሆነ ብዙ የአ​ካል ክፍ​ሎ​ችም እንደ አሉ​በት፥ ነገር ግን የአ​ካል ክፍ​ሎች ሁሉ ብዙ​ዎች ሳሉ አንድ አካል እንደ ሆኑ ክር​ስ​ቶስ ደግሞ እን​ዲሁ ነው፤


ንጉሡም መልሶ ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት፤’ ይላቸዋል።


በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ ወደ እርሱ ቀርቦ “ጌታ ሆይ! ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ልተውለት? እስከ ሰባት ጊዜን?” አለው።


“ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁና።


እነሆ፥ ዛሬ በዋ​ሻው ውስጥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጄ አሳ​ልፎ እንደ ሰጠህ ዐይ​ንህ አይ​ታ​ለች፤ አን​ተ​ንም እን​ድ​ገ​ድ​ልህ ሰዎች ተና​ገ​ሩኝ፤ እኔ ግን፦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀባ ነውና እጄን በጌ​ታዬ ላይ አል​ዘ​ረ​ጋም ብዬ ራራ​ሁ​ልህ።


ሰውስ ሰውን ቢበ​ድል ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ል​ዩ​ለ​ታል፤ ሰው ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቢበ​ድል ስለ እርሱ ወደ ማን ይጸ​ል​ዩ​ለ​ታል?” እነ​ርሱ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ጠ​ፋ​ቸው ወድ​ዶ​አ​ልና የአ​ባ​ታ​ቸ​ውን ቃል አል​ሰ​ሙም።


ሙሴም አሮ​ንን፥ “ይህን ታላቅ ኀጢ​አት ታመ​ጣ​በት ዘንድ ይህ ሕዝብ ምን አደ​ረ​ገህ?” አለው።


ሙሴም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያን​ጐ​ራ​ጐ​ራ​ች​ሁ​በ​ትን ማን​ጐ​ራ​ጐ​ራ​ች​ሁን ሰም​ቶ​አ​ልና በመሸ ጊዜ ትበሉ ዘንድ ሥጋን፥ በማ​ለ​ዳም ትጠ​ግቡ ዘንድ እን​ጀ​ራን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሰ​ጣ​ች​ኋል፤ እኛም ምን​ድን ነን? ማን​ጐ​ራ​ጐ​ራ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ነው እንጂ በእኛ ላይ አይ​ደ​ለም” አለ።


ሮቤ​ልም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ብላ​ቴ​ና​ውን አት​በ​ድሉ ብዬ​አ​ችሁ አል​ነ​በ​ረ​ምን? እኔ​ንም አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ኝም፤ ስለ​ዚህ እነሆ፥ አሁን ደሙ ይፈ​ላ​ለ​ጋ​ች​ኋል።”


አቤ​ሜ​ሌ​ክም አብ​ር​ሃ​ምን ጠርቶ አለው፥ “ይህ ያደ​ረ​ግ​ህ​ብን ምን​ድን ነው? ምንስ ክፉ ሠራ​ሁ​ብህ? በእ​ኔና በመ​ን​ግ​ሥቴ ላይ ትልቅ ኀጢ​አት አው​ር​ደ​ሃ​ልና፤ ማንም የማ​ያ​ደ​ር​ገው የማ​ይ​ገባ ሥራ በእኔ ሠራ​ህ​ብኝ።”


“በእኔም ከሚያምኑት ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ ትልቅ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይሻለው ነበር።


ከእ​ነ​ዚህ ከታ​ና​ና​ሾቹ አን​ዱን ከሚ​ያ​ሰ​ና​ክል ይልቅ አህያ የሚ​ፈ​ጭ​በት የወ​ፍጮ ድን​ጋይ በአ​ን​ገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር ቢሰ​ጥም በተ​ሻ​ለው ነበር።


በመ​ብል ምክ​ን​ያት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍጥ​ረት አና​ፍ​ርስ፤ ለን​ጹ​ሓን ሁሉ ንጹሕ ነው፤ ለሰ​ውስ ክፉው ነገር በመ​ጠ​ራ​ጠር መብ​ላት ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios