Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 2:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እኛ የዚ​ህን ዓለም መን​ፈስ የተ​ቀ​በ​ልን አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጠ​ንን ጸጋ እና​ውቅ ዘንድ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሆ​ነ​ውን መን​ፈስ ተቀ​በ​ልን።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ፣ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንምና፤ ይህም እግዚአብሔር በነጻ የሰጠንን እናውቅ ዘንድ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እኛ ግን፥ እናውቅ ዘንድ ከእግዚአብሔር በነፃ የተሰጠንን፥ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ከእግዚአብሔር የተሰጠንን ነገር እንድናውቅ የእግዚአብሔርን መንፈስ እንጂ የዚህን ዓለም መንፈስ አልተቀበልንም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እኛ ግን ከእግዚአብሔር እንዲያው የተሰጠንን እናውቅ ዘንድ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንም።

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 2:12
17 Referencias Cruzadas  

እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ።


እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ።


እን​ግ​ዲህ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ላሉት በመ​ን​ፈስ እንጂ በሥጋ ለማ​ይ​መ​ላ​ለሱ ፍርድ የለ​ባ​ቸ​ውም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​መ​ስ​ለው የክ​ር​ስ​ቶስ የክ​ብሩ ወን​ጌል ብር​ሃን እን​ዳ​ያ​በ​ራ​ላ​ቸው የዚህ ዓለም አም​ላክ ልባ​ቸ​ውን አሳ​ው​ሮ​አ​ልና።


ወይስ መጽሐፍ “በእኛ ዘንድ ያሳደረው መንፈስ በቅንዓት ይመኛል፤” ያለው በከንቱ እንደ ተናገረ ይመስላችኋልን?


ለልጁ ስንኳ አል​ራ​ራም፤ ስለ ሁላ​ችን ቤዛ አድ​ርጎ አሳ​ልፎ ሰጠው እንጂ፥ እን​ግ​ዲህ እርሱ ሁሉን እን​ዴት አይ​ሰ​ጠ​ንም?


እርሱም “እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸው፤ የነቢያትም መናፍስት ጌታ አምላክ በቶሎ ሊሆን የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ እንዲያሳይ መልአኩን ሰደደ።”


ጳው​ሎ​ስም ቢሆን፥ አጵ​ሎ​ስም ቢሆን፥ ጴጥ​ሮ​ስም ቢሆን፥ ዓለ​ምም ቢሆን፥ ሕይ​ወ​ትም ቢሆን፥ ሞትም ቢሆን፥ ያለ​ውም ቢሆን፥ የሚ​መ​ጣ​ውም ቢሆን ሁሉ የእ​ና​ንተ ነው።


ይኸ​ውም ቀድሞ በዚህ ዓለም ሥር​ዐት፥ አሁን በከ​ሓ​ድ​ያን ልጆች የሚ​በ​ረ​ታ​ታ​ባ​ቸ​ውና፥ በነ​ፋስ አም​ሳል የሚ​ገ​ዛ​ቸው አለቃ እንደ ነበ​ረው ፈቃድ ጸን​ታ​ችሁ የነ​በ​ራ​ች​ሁ​በት ነው።


ለዐ​ዋ​ቆች ጥበ​ብን እን​ነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለን፤ ነገር ግን የዚ​ህን ዓለም ጥበብ ወይም ያልፉ ዘንድ ያላ​ቸ​ውን የዚ​ህን ዓለም ሹሞች ጥበብ አይ​ደ​ለም።


ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበ​በ​ኞ​ችን ሊያ​ሳ​ፍር የዚ​ህን ዓለም ሰነ​ፎች መረጠ፤ ኀይ​ለ​ኞ​ች​ንም ያሳ​ፍር ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዚ​ህን ዓለም ደካ​ሞች መረጠ።


ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ፤ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios