Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 15:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ሁሉን ከእ​ግሩ በታች አስ​ገ​ዝ​ቶ​ለ​ታ​ልና፥ “ሁሉ ይገ​ዛ​ለት” ባለ ጊዜ ግን ሁሉን ከሚ​ያ​ስ​ገ​ዛ​ለት በቀር እንደ ሆነ የታ​ወቀ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 “ሁሉን ከእግሩ በታች አስገዛህለት”፤ ነገር ግን፣ “ሁሉን አስገዛለት” ሲል፣ ሁሉን ካስገዛለት በቀር መሆኑ ግልጽ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 “ሁሉን ነገር ከእግሩ ሥር አስገዝቶለታል” ተብሏልና፤ ነገር ግን፥ ሁሉን ነገር አስገዛለት ሲል፥ ሁሉ ነገር በክርስቶስ ሥር እንዲገዛ ያደረገውን እግዚአብሔርን እንደማይጨምር ግልጽ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 “እግዚአብሔር ሁሉን ነገር በሥልጣኑ ሥር አድርጎለታል” የሚል ተጽፎአል፤ ነገር ግን “ሁሉ ነገር በሥልጣኑ ሥር ሆኖአል” ሲባል ሁሉን ነገር በሥልጣኑ ሥር ያደረገለትን እግዚአብሔር አብን አይጨምርም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ሁሉን ከእግሩ በታች አስገዝቶአልና። ነገር ግን፦ ሁሉ ተገዝቶአል ሲል፥ ሁሉን ካስገዛለት በቀር መሆኑ ግልጥ ነው።

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 15:27
14 Referencias Cruzadas  

በእ​ጆ​ች​ህም ሥራ ሁሉ ላይ ሾም​ኸው፤ ሁሉን ከእ​ግ​ሮቹ በታች አስ​ገ​ዛ​ህ​ለት፥


ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፤ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም።


ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ አብ ሁሉን በእጁ እንደ ሰጠው፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ወጣ፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ደ​ሚ​ሄድ ባወቀ ጊዜ፥


አብ ልጁን ይወ​ዳ​ልና፥ ሁሉን በእጁ ሰጠው።


ከሙ​ታን ለይቶ ባስ​ነ​ሣው፥ በሰ​ማ​ይም በቀኙ ባስ​ቀ​መ​ጠው፥


ሁሉ​ንም ከእ​ግሩ በታች አድ​ርጎ አስ​ገ​ዛ​ለት፤ ከሁሉ በላይ የሆነ እር​ሱን ለቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ራስ አደ​ረ​ገው።


ከሆነ ጀምሮ ከመ​ላ​እ​ክት፥ “ጠላ​ቶ​ች​ህን ከእ​ግ​ርህ ጫማ በታች እስከ አደ​ር​ግ​ልህ ድረስ በቀኜ ተቀ​መጥ” ማንን አለው?


እርሱ ግን ስለ ኀጢ​አት አን​ድን መሥ​ዋ​ዕት ለዘ​ለ​ዓ​ለም አቅ​ርቦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀኝ ተቀ​መጠ።


ሁሉ​ንም ከእ​ግሩ በታች አድ​ር​ገህ አስ​ገ​ዛ​ህ​ለት።” ሁሉን ለእ​ርሱ ባስ​ገ​ዛ​ለት ጊዜም የተ​ወ​ውና ያላ​ስ​ገ​ዛ​ለት የለም፤ አሁን ግን ሁሉን እን​ዳ​ስ​ገ​ዛ​ለት አና​ይም።


እርሱም መላእክትና ሥልጣናት ኀይላትም ከተገዙለት በኋላ ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር ቀኝ አለ።


ሕያውም እኔ ነኝ፤ ሞቼም ነበርሁ፤ እነሆም ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፤ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos