Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 91:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በላባዎቹ ይጋርድሃል፤ በክንፎቹ ሥር መሸሸጊያ ታገኛለህ፤ ታማኝነቱ ጋሻና መከታ ይሆንሃል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በላባዎቹ ይጋርድሃል፥ ከክንፎቹም በታች ትጠለላለህ፥ ታማኝነቱ እንደ ጋሻና እንደ ቅጥር ይከብብሃል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በጥበቃው ሥር ያደርግሃል። እርሱ ስለሚንከባከብህ በሰላም ትኖራለህ፤ የእርሱ ታማኝነት እንደ ጋሻ ወይም እንደ ከተማ ቅጽር ይሆንልሃል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 አቤቱ፥ በሥ​ራህ ደስ አሰ​ኝ​ተ​ኸ​ኛ​ልና፤ በእ​ጆ​ች​ህም ሥራ ደስ ይለ​ኛ​ልና።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 91:4
14 Referencias Cruzadas  

በድንኳንህ ለዘላለም ልኑር፤ በክንፎችህም ጥላ ልከለል። ሴላ


ማረኝ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ማረኝ፤ ነፍሴ አንተን መጠጊያ አድርጋለችና፤ በክንፎችህ ሥር እጠለላለሁ።


እንደ ዐይንህ ብሌን ጠብቀኝ፤ በክንፎችህም ጥላ ሰውረኝ፤


ንስር ጐጆዋን በትና፣ በጫጩቶቿም ላይ እንደምትረብብ፣ እነርሱን ለመያዝ ክንፎቿን እንደምትዘረጋ፣ በክንፎቿም እንደምትሸከማቸው፣


ትልቁንና ትንሹን ጋሻ ያዝ፤ እኔንም ለመርዳት ተነሥ።


ከዚህም በኋላ፣ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል በራእይ ወደ አብራም መጣ፤ “አብራም ሆይ፤ አትፍራ፤ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፤ ታላቅ ዋጋህም እኔው ነኝ።”


“ኢየሩሳሌም፣ ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ነቢያትን የምትገድዪ፣ ወደ አንቺ የተላኩትንም በድንጋይ የምትወግሪ፤ ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ ሥር እንደምትሰበስብ፣ ልጆችሽን ለመሰብሰብ ስንት ጊዜ ፈለግሁ፤ እናንተ ግን አልፈቀዳችሁም፤


ስላደረግሽው ሁሉ እግዚአብሔር ዋጋሽን ይክፈልሽ፤ በክንፉ ጥላ ሥር ለመጠለል የመጣሽበት የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ብድራትሽን አትረፍርፎ ይመልስልሽ።”


እምነቱና ዕውቀቱ የተመሠረቱትም የማይዋሸው አምላክ ከዘመናት በፊት በገባው የዘላለም ሕይወት ተስፋ ላይ ነው።


ሰማይና ምድር ያልፋሉ፣ ቃሌ ግን አያልፍም።


ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ፤ ስለ ምሕረትህና ስለ ታማኝነትህ፣ ለስምህ ምስጋና አቀርባለሁ፤ ስምህንና ቃልህን፣ ከሁሉ በላይ ከፍ ከፍ አድርገሃልና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios