Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 85:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ምሕረትና ታማኝነት ተገናኙ፤ ጽድቅና ሰላም ተቃቀፉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ነገር ግን ክብር በምድራችን ያድር ዘንድ ማዳኑ ለሚፈሩት ቅርብ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ፍቅርና እውነት ይተቃቀፋሉ፤ ጽድቅና ሰላም ይስማማሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 አቤቱ፥ ድን​ቅን የም​ታ​ደ​ርግ አንተ ታላቅ ነህና፥ አን​ተም ብቻ​ህን ታላቅ አም​ላክ ነህና፥

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 85:10
17 Referencias Cruzadas  

ፍቅርና ታማኝነት ከቶ አይለዩህ፤ በዐንገትህ ዙሪያ እሰራቸው፤ በልብህም ጽላት ላይ ጻፋቸው።


ጽድቅና ፍትሕ የዙፋንህ መሠረቶች ናቸው፤ ምሕረትና ታማኝነት በፊትህ ይሄዳሉ።


ሕግ በሙሴ በኩል ተሰጥቶ ነበር፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል መጣ።


እግዚአብሔር ቸር፣ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና፤ ታማኝነቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው።


ይህም የሆነው ኀጢአት በሞት እንደ ነገሠ ሁሉ፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ደግሞ የዘላለም ሕይወት ይገኝ ዘንድ ጸጋ በጽድቅ እንዲነግሥ ነው።


ተራሮች ብልጽግናን፣ ኰረብቶችም የጽድቅን ፍሬ ለሕዝቡ ያመጣሉ።


ከቀድሞ ዘመን ጀምሮ ለአባቶቻችን በመሐላ ቃል እንደ ገባህላቸው፣ ለያዕቆብ ታማኝነትን፣ ለአብርሃምም ምሕረትን ታደርጋለህ።


ስለ እኔም ሲናገሩ፣ ‘ጽድቅና ኀይል፣ በእግዚአብሔር ብቻ ነው’ ይላሉ።” በርሱ ላይ በቍጣ የተነሡ ሁሉ፣ ወደ እርሱ መጥተው ያፍራሉ።


አብርሃምም ከሁሉ ነገር ዐሥራትን አውጥቶ ሰጠው። በመጀመሪያ ስሙ “የጽድቅ ንጉሥ” ማለት ነው፤ ኋላም ደግሞ “የሳሌም ንጉሥ” ማለትም “የሰላም ንጉሥ ማለት” ነው።


እንግዲህ በእምነት ስለ ጸደቅን፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከእግዚአብሔር ጋራ ሰላም አለን።


“ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም፣ ሰላምም እርሱ ለሚወድዳቸው ሰዎች በምድር ይሁን!”


ጽድቄን እያመጣሁ ነው፤ ሩቅም አይደለም፤ ማዳኔም አይዘገይም። ለጽዮን ድነትን፣ ለእስራኤል ክብሬን አጐናጽፋለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios