Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 8:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በሐሳብህ ስፍራ ትሰጠው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ትጠነቀቅለትም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 የጣቶችህን ሥራ ሰማዮችህን ባየሁ ጊዜ፥ ጨረቃንና ከዋክብትን አንተ የሠራሃቸውን፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 አንተ እርሱን ታስበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? እርሱንስ ትጐበኘው ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ታስ​በው ዘንድ ሰው ምን​ድን ነው? ትጐ​በ​ኘ​ውም ዘንድ የሰው ልጅ ምን​ድን ነው?

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 8:4
25 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህን ያህል በልብህ ስፍራ ትሰጠው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ታስበውስ ዘንድ የሰው ልጅ እስከዚህ ምንድን ነው?


“ከፍ ከፍ ታደርገው ዘንድ፣ ልብህንም ትጥልበት ዘንድ ሰው ምንድን ነው?


በገዦች አትታመኑ፤ ማዳን በማይችሉ በሰው ልጆችም አትመኩ።


“በውኑ እግዚአብሔር ከሰው ጋራ በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ፤ ሰማያትና ሰማየ ሰማያት እንኳ አንተን ሊይዙህ አይችሉም፤ ታዲያ እኔ የሠራሁት ይህ ቤተ መቅደስማ ምንኛ ያንስ!


“የእስራኤል አምላክ፣ ጌታ ይመስገን፤ መጥቶ ሕዝቡን ተቤዥቷልና።


ኢየሱስም፣ “ቀበሮዎች ጕድጓድ፣ የሰማይ ወፎችም ጐጆ አላቸው፤ የሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት ቦታ የለውም” ሲል መለሰለት።


ለራስህ ባበረታኸው የሰው ልጅ ላይ፣ በቀኝ እጅህ ሰው ላይ እጅህ ትሁን።


ይልቁን ከብል የሚቈጠር የሰው ልጅ፣ ትል የሆነውማ ሰው ምንኛ ያንስ!”


“የማጽናናችሁ እኔ፣ እኔው ብቻ ነኝ፤ ሟች የሆኑትን ሰዎች፣ እንደ ሣር የሚጠወልጉትን የሰው ልጆች ለምን ትፈራለህ?


እግዚአብሔር ሆይ፤ ለሕዝብህ ሞገስ ስታድል ዐስበኝ፤ በምታድናቸውም ጊዜ ርዳኝ፤


እግዚአብሔር በተናገረው መሠረት ሣራን ዐሰባት፤ የገባውንም ተስፋ ፈጸመላት።


አሕዛብ ሁሉ በፊቱ እንደ ኢምንት ናቸው፤ ከምንም የማይቈጠሩ መና ናቸው።


አንቺንና በቅጥርሽ ውስጥ የሚኖሩትንም ልጆችሽን ከዐፈር ይደባልቃሉ፤ ድንጋይም በድንጋይ ላይ አይተዉም፤ የመጐብኛሽን ጊዜ አላወቅሽምና።”


እርሱም፣ “የሰው ልጅ ሆይ፤ ይህን አይተሃልን? ከዚህም የባሰ አስጸያፊ ነገር ታያለህ” አለኝ።


ሰዎች ሆይ፤ እስከ መቼ ድረስ ክብሬን ዝቅ ታደርጋላችሁ? እስከ መቼስ ድረስ ከንቱ ነገርን ትወድዳላችሁ? ሐሰትንስ ትሻላችሁ? ሴላ


ሕዝቡም አመኑ፣ እግዚአብሔር የእስራኤልን ልጆች እንደ ጐበኛቸውና መከራቸውን እንዳየ በሰሙ ጊዜ ተንበረከኩ፤ በስግደትም አመለኩት።


ምንም እንኳ ክፉ እንደምትሠሩ አድርገው ቢያሟችሁም፣ ለፍርድ በሚመጣበት ጊዜ መልካሙን ሥራችሁን አይተው እግዚአብሔርን እንዲያከብሩ፣ በአሕዛብ መካከል በመልካም ሕይወት ኑሩ።


በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ።


ከዚያም እግዚአብሔር፣ “ቀኑን ከሌሊት እንዲለዩ፣ የዓመት ወቅቶች፣ ቀናትና ዓመታት የሚጀምሩበትንም እንዲያመለክቱ፣


በዚያችም ምሽት ደግሞ አባታቸውን የወይን ጠጅ አጠጡት፤ ትንሿ ልጁም ሄዳ ከአባቷ ጋራ ተኛች፤ እርሱ ግን ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቀም ነበር።


ቀን ለሌላው ቀን ይናገራል፤ ሌሊትም ለሌሊት ዕውቀትን ይገልጣል፤


የአሕዛብ አማልክት ሁሉ ጣዖታት ናቸው፤ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ።


ሰማያትን በብልኀት የሠራ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።


ጨረቃና ከዋክብት በሌሊት እንዲሠለጥኑ ያደረገ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios