Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 7:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ተንኰሉ ወደ ራሱ ይመለሳል፤ ዐመፃውም በገዛ ዐናቱ ላይ ይወርዳል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ጉድጓድን ማሰ ቈፈረም። በሠራውም ጉድጓድ ይወድቃል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 የሚያመጡት ችግር በራሳቸው ላይ ይደርሳል፤ በክፉ ድርጊታቸውም ዐናታቸው ይፈጠፈጣል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ጉዳቱ በራሱ ይመ​ለ​ሳል፥ ዐመ​ፃ​ውም በአ​ናቱ ላይ ትወ​ር​ዳ​ለች።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 7:16
21 Referencias Cruzadas  

ሤራው በንጉሡ ዘንድ እንደ ታወቀ ሐማ በአይሁድ ላይ የሸረበው ሤራ በገዛ ራሱ ላይ እንዲጠመጠም፣ እርሱና ወንዶች ልጆቹም በዕንጨት ላይ እንዲሰቀሉ የጽሑፍ ትእዛዝ አስተላለፈ።


አባቴ ዳዊት ሳያውቅ ኢዮአብ በሁለቱ ሰዎች ላይ አደጋ ጥሎ በሰይፍ ገድሏቸዋልና ስላፈሰሰው ደም እግዚአብሔር ይበቀለዋል። የእስራኤል ሰራዊት አዛዥ የኔር ልጅ አበኔርና የይሁዳ ሰራዊት አዛዥ የዬቴር ልጅ አሜሳይ ሁለቱም ከርሱ የተሻሉና ይበልጥ ትክክለኛ ሰዎች ነበሩ።


ክፉ አድራጊዎች እንዴት እንደ ወደቁና እንደ ተጋደሙ፣ ቍልቍልም እንደ ተወረወሩና መነሣት እንደማይችሉ ተመልከት!


እግዚአብሔር አንተንና እስራኤልን ለፍልስጥኤማውያን አሳልፎ ይሰጣል፤ አንተና ልጆችህም ነገ ከእኔ ጋራ ትሆናላችሁ፤ እንዲሁም እግዚአብሔር የእስራኤልን ሰራዊት ለፍልስጥኤማውያን አሳልፎ ይሰጣል።”


ሕያው እግዚአብሔርን! እግዚአብሔር ራሱ ይቀሥፈዋል፤ ወይም ቀኑ ደርሶ ይሞታል፤ ወይም በጦርነት ይሞታል።


ዳዊትም ሳኦል ክፉ እንዳሰበበት ባወቀ ጊዜ፣ ካህኑን አብያታርን፣ “ኤፉዱን አምጣ” አለው።


በመኝታው ላይ ክፋትን ያውጠነጥናል፤ ራሱን በጎ ባልሆነ መንገድ ይመራል፤ ክፋትንም አያርቅም።


እንዲህም በለው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ሰውየውን ገደልኸው፤ ደግሞ ርስቱን ልትወስድ?’ ከዚያም እንዲህ በለው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ውሾች የናቡቴን ደም በላሱበት ቦታ የአንተንም ደም ውሾች እንዲሁ ይልሱታል!’ ”


ስለዚህ ለመርዶክዮስ ባዘጋጀው ግንድ ላይ ሐማን ሰቀሉት፤ ከዚያም የንጉሡ ቍጣ በረደ።


እኔ እንዳየሁ ክፋትን የሚያርሱ፣ መከራንም የሚዘሩ ያንኑ ያጭዳሉ።


እግዚአብሔር በትክክለኛ ፍርዱ የታወቀ ነው፤ ክፉዎችም በእጃቸው ሥራ ተጠመዱ። ሒጋዮን ሴላ


ያልታሰበ ጥፋት ይምጣባቸው፤ የሰወሩት ወጥመድ ይያዛቸው፤ ይጠፉም ዘንድ ወደ ጕድጓዱ ይውደቁ።


እግዚአብሔር ሆይ፤ ልቤ ጽኑ ነው፤ ልቤ ጽኑ ነው፤ እቀኛለሁ፤ እዘምራለሁ።


እኔ ብቻ በደኅና ሳመልጥ፣ ክፉዎቹ በገዛ ወጥመዳቸው ይውደቁ።


ያላግባብ ለጥቅም የሚሯሯጡ ሁሉ መጨረሻቸው እንዲህ ነው፤ የሕይወታቸው መጥፊያም ይኸው ነው።


ጕድጓድ የሚምስ ራሱ ይገባበታል፤ ድንጋይ የሚያንከባልልም ተመልሶ በላዩ ላይ ይገለበጥበታል።


ጕድጓድን የሚምስ ራሱ ይገባበታል፤ ቅጥርንም የሚያፈርስ እባብ ይነድፈዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios