Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 68:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 በበጎች በረት መካከል ብትገኙ እንኳ፣ ከብር እንደ ተሠሩ የርግብ ክንፎች፣ በቅጠልያ ወርቅ እንደ ተለበጡ ላባዎች ናችሁ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 የሠራዊት ነገሥታት ፈጥነው ይሸሻሉ፥ በቤትም የምትኖር ምርኮን ተካፈለች።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 በጎቹን ለመጠበቅ ወደ ኋላ የቀሩት ክንፎቻቸው በብር የተለበዱ አንጸባራቂ የሆኑ ከወርቅ የተሠሩ ላባ ያላቸው ማዕድናዊ ርግቦችን አገኙ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እኔስ በጸ​ሎቴ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ር​ታው በጊ​ዜው ነው፤ ይቅ​ር​ታህ ብዙ ሲሆን መድ​ኃ​ኒቴ ሆይ፥ በእ​ው​ነት አድ​ነኝ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 68:13
22 Referencias Cruzadas  

የእስራኤልንም ሕዝብ ብርና ወርቅ ጭኖ እንዲወጣ አደረገ፤ ከነገዶቻቸውም አንድም አልተደናቀፈም።


“ይሳኮር፣ በበጎች ጕረኖም መካከል የሚተኛ ዐጥንተ ብርቱ አህያ ነው።


ቀደም ሲል እኛ ራሳችን ማስተዋል የጐደለን፣ የማንታዘዝ፣ የተታለልን፣ ለተለያየ ምኞትና ምቾት ባሪያ ሆነን የተገዛን ነበርን፤ እየተጣላንና እርስ በርስ እየተጠላላን በክፋትና በምቀኛነት እንኖር ነበር።


“አባቱ ግን ባሮቹን እንዲህ አላቸው፤ ‘ፈጥናችሁ ከሁሉ ምርጥ የሆነውን ልብስ አምጡና አልብሱት፤ ለጣቱ ቀለበት፣ ለእግሩም ጫማ አድርጉለት፤


ዐሣማዎቹ የሚመገቡትን ዐሠር እንኳ ለመብላት ይመኝ ነበር፤ ነገር ግን ይህን እንኳ የሚሰጠው ሰው አልነበረም።


እግዚአብሔር በሕዝቡ ደስ ይለዋልና፤ የዋሃንንም በማዳኑ ውበት ያጐናጽፋል።


“ትከሻውን ከሸክም ገላገልሁት፤ እጁንም ቅርጫት ከመያዝ አሳረፍሁ።


የርግብህን ነፍስ አሳልፈህ ለዱር አራዊት አትስጥ፤ የችግረኞች ሕዝብህን ሕይወት ለዘላለሙ አትርሳ።


በበጎች ጕረኖ መካከል ለምን ተቀመጥህ? መንጎችን የሚጠራውን ፉጨት ለመስማት ነውን? በሮቤል አውራጃዎች፣ ብዙ የልብ ምርምር ነበር።


ጭቃ በማስቦካት፣ ጡብ በማሠራትና በዕርሻም ሁሉ እያስጨነቁ ከባድ ሥራ እንዲሠሩ በማድረግ ሕይወታቸውን አስመረሩ፤ ግብጻውያኑ በሚያሠሯቸው ከባድ ሥራ ሁሉ ፈጽሞ አይራሩላቸውም ነበር።


አረማውያን በነበራችሁበት ጊዜ ወዲያና ወዲህ በመነዳት ድዳ ወደ ሆኑ ጣዖታት እንደ ተወሰዳችሁ ታውቃላችሁ።


ምርኮውንም ለሁለት ከፍላችሁ በጦርነቱ ለተካፈሉት ወታደሮችና ለቀረው ማኅበረ ሰብ አከፋፍሉት።


በዚህ ጊዜ ዐምስቱ የአሞራውያን ነገሥታት ሸሽተው በመቄዳ ዋሻ ተደብቀው ነበር።


“ነገሥታት መጡ፤ ተዋጉም፤ የከነዓን ነገሥታት፣ በመጊዶ ውሆች አጠገብ በታዕናክ ተዋጉ፤ ብርም ሆነ ሌላ ምርኮ ተሸክመው አልሄዱም።


ከዚያም ሕዝቡ ወጥቶ የሶርያውያንን ሰፈር በዘበዘ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው አንድ መስፈሪያ ማለፊያ ዱቄት በአንድ ሰቅል፣ ሁለት መስፈሪያ ገብስም በአንድ ሰቅል ተሸጠ።


መወጠሪያ ገመድህ ላልቷል፤ ምሰሶው ጠብቆ አልተተከለም፤ ሸራው አልተወጠረም፤ በዚያ ጊዜ ታላቅ ምርኮ ይከፋፈላል፤ ዐንካሳ እንኳ ሳይቀር ምርኮ ይወስዳል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios