18 ኀጢአትን በልቤ አስተናግጄ ቢሆን ኖሮ፣ ጌታ ባልሰማኝ ነበር።
18 በልቤስ በደልን አይቼ ብሆን ጌታ አይሰማኝም ነበር።
18 ኃጢአቴን ሳልናዘዝ በልቤ ሰውሬ ቢሆን ኖሮ፥ እግዚአብሔር ጸሎቴን ባልሰማም ነበር።
እግዚአብሔር የሚሰማው፣ የሚፈራውንና ፈቃዱን የሚያደርገውን እንጂ፣ ኀጢአተኞችን እንደማይሰማ እናውቃለን፤
ሕግን ላለመስማት ጆሮውን የሚደፍን፣ ጸሎቱ እንኳ አስጸያፊ ነው።
እግዚአብሔር ከክፉዎች ሩቅ ነው፤ የጻድቃንን ጸሎት ግን ይሰማል።
እግዚአብሔር የክፉዎችን መሥዋዕት ይጸየፋል፤ የቅኖች ጸሎት ግን ደስ ያሠኘዋል።
እጆቻቸሁን ለጸሎት ወደ እኔ ስትዘረጉ፣ ዐይኖቼን ከእናንተ እሰውራለሁ፤ አብዝታችሁ ብትጸልዩም እንኳ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ በደም ተበክለዋል፤
ትለምናላችሁ ግን አትቀበሉም፣ ለራሳችሁ ሥጋዊ ደስታ በማሰብ በክፉ ምኞት ትለምናላችሁና።
ሰው የድኾችን ጩኸት ላለመስማት ጆሮውን ቢዘጋ፣ እርሱም ይጮኻል፤ መልስም አያገኝም።
ከመከራ ይልቅ መርጠኸዋልና፣ ወደ ክፋት እንዳትመለስ ተጠንቀቅ።
በርግጥ እግዚአብሔር ከንቱ ጩኸታቸውን አይሰማም፤ ሁሉን ቻይ አምላክ አያዳምጣቸውም።