Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 66:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ሰዎች በራሳችን ላይ እንዲፈነጩ አደረግህ፤ በእሳትና በውሃ መካከል ዐለፍን፤ የኋላ ኋላ ግን ወደ በረከት አመጣኸን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ሰው በራሳችን ላይ እንዲረማመድ አደረግህ፥ በእሳትና በውኃ መካከል አለፍን፥ ወደ በረከትም አወጣኸን።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ጠላቶቻችን በግፍ እንዲረግጡን አደረግህ፤ በእሳትና በጐርፍ መካከል አለፍን፤ አሁን ግን ብልጽግና ወደ መላበት ወደ ሰፊ ቦታ አመጣኸን።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 66:12
16 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ ንጉሡ መላውን ሕዝብ አስከትሎ ወጣ፤ ጥቂት ርቀው ከሄዱ በኋላም በአንዲት ቦታ ቆሙ።


“አንተንም ከመከራ መንጋጋ፣ ጭንቀት ወደሌለበት ወደ ሰፊ ስፍራ፣ ምርጥ ምግብ ወደ ሞላበት ማእድ ያወጣሃል።


እርሱ ከስድስት መቅሠፍት ይታደግሃል፤ በሰባተኛውም ጕዳት አያገኝህም።


በዚህም ነፍሳቸውን ከሞት ያድናል፤ በራብ ዘመንም በሕይወት ያኖራቸዋል።


ባስጨነቁሽ፣ ‘በላይሽ ላይ እንድንሄድ ተነጠፊልን’ ባሉሽ እጅ ላይ አደርገዋለሁ፤ ጀርባሽን እንደ መሬት፣ እንደ መሸጋገሪያም መንገድ አደረግሽላቸው።”


ናቡከደነፆርም ወደሚነድደው የእቶን እሳት በር ቀረብ ብሎ ከፍ ባለ ድምፅ፣ “እናንተ የልዑል አምላክ አገልጋዮች ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎ፤ ኑ ውጡ! ወደዚህ ኑ!” አላቸው። ስለዚህ ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብድናጎ ከእሳቱ ወጡ፤


“አብርሃም ግን እንዲህ አለው፤ ‘ልጄ ሆይ፤ አንተ በምድራዊ ሕይወትህ ዘመን መልካም ነገሮችን እንደ ተቀበልህ፣ አልዓዛርም ደግሞ ክፉ ነገሮችን እንደ ተቀበለ አስታውስ፤ አሁን ግን እርሱ እዚህ ሲጽናና፣ አንተ በሥቃይ ላይ ትገኛለህ።


የደቀ መዛሙርቱንም ልብ በማበረታታትና በእምነታቸው ጸንተው እንዲኖሩ በመምከር፣ “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት በብዙ መከራ ማለፍ አለብን” አሏቸው።


በትዕግሥት የጸኑትን የተባረኩ አድርገን እንደምንቈጥር ታውቃላችሁ፤ ኢዮብ እንዴት ታግሦ እንደ ጸና ሰምታችኋል፤ ጌታም በመጨረሻ ያደረገለትን አይታችኋል። ጌታ እጅግ ርኅሩኅና መሓሪ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos