Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 4:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ስትቈጡ ኀጢአት አትሥሩ፤ በዐልጋችሁም ላይ ሳላችሁ፣ ልባችሁን መርምሩ፤ ጸጥም በሉ። ሴላ

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በጻድቁ እንደ ተገለጠ እወቁ፥ ጌታ ወደ እርሱ በተጣራሁ ጊዜ ይሰማኛል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ምንም ያኽል ብትበሳጩ ኃጢአት አትሥሩ፤ በምትተኙበት ስፍራ በጸጥታ ልባችሁን መርምሩ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ተቈጡ፥ ነገር ግን አት​በ​ድሉ፤ በመ​ኝ​ታ​ችሁ ሳላ​ችሁ በል​ባ​ችሁ የም​ታ​ስ​ቡት ይታ​ወ​ቃ​ችሁ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 4:4
17 Referencias Cruzadas  

ከዚያም ሰውን፣ ‘እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፤ ከክፋትም መራቅ ማስተዋል ነው’ አለው።”


ገዦች ያለ ምክንያት አሳደዱኝ፤ ልቤ ግን ከቃልህ የተነሣ እጅግ ፈራ።


አምላክ ሆይ፤ ስለምትመልስልኝ አንተን እጣራለሁ፤ ጆሮህን ወደ እኔ ጣል አድርገህ ጸሎቴን ስማ።


እግዚአብሔርን በፍርሀት አገልግሉት፤ ለርሱ በመንቀጥቀጥ ደስ ያሰኛችሁ።


ብዙዎች ነፍሴን፣ “እግዚአብሔር አይታደግሽም” አሏት። ሴላ


ወደ እግዚአብሔር ድምፄን ከፍ አድርጌ እጮኻለሁ፤ እርሱም ከተቀደሰ ተራራው ይመልስልኛል። ሴላ


ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን ትፍራው፤ በዓለም የሚኖር ሕዝብ ሁሉ በፊቱ ይንቀጥቀጥ።


“ዕረፉ፤ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ ዕወቁ፤ በሕዝቦች ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፤ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።”


በመኝታዬ ዐስብሃለሁ፤ ሌሊቱንም ሁሉ ስለ አንተ አሰላስላለሁ።


ዝማሬዬን በሌሊት አስታወስሁ፤ ከልቤም ጋራ ተጫወትሁ፤ መንፈሴም ተነቃቅቶ እንዲህ ሲል ጠየቀ፤


የቅኖች ጐዳና ከክፋት የራቀ ነው፤ መንገዱንም የሚጠብቅ ሕይወቱን ይጠብቃል።


በፍቅርና በታማኝነት ኀጢአት ይሰረያል፤ እግዚአብሔርን በመፍራት ሰው ከክፋት ይርቃል።


በራስህ አስተያየት ጠቢብ ነኝ አትበል፤ እግዚአብሔርን ፍራ፤ ከክፉም ራቅ።


ልትፈሩኝ አይገባችሁምን?” ይላል እግዚአብሔር፤ “በእኔ ፊት ልትንቀጠቀጡስ አይገባምን? ለዘላለም ዐልፎት መሄድ እንዳይችል፣ አሸዋን ለባሕር ድንበር አደረግሁ፤ ማዕበሉ እየጋለበ ቢመጣ ከዚያ አያልፍም፤ ሞገዱ ቢጮኽም ሊያቋርጠው አይችልም።


እግዚአብሔር ግን በተቀደሰ መቅደሱ አለ፤ ምድር ሁሉ በፊቱ ጸጥ ትበል።


በእምነት መሆናችሁን ለማወቅ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ። ከፈር የወጣችሁ ካልሆነ በቀር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በውስጣችሁ እንዳለ አታውቁምን?


“ተቈጡ፤ ነገር ግን ኀጢአት አትሥሩ፤” በቍጣችሁ ላይ ፀሓይ አይግባ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos