Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 22:29 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 የምድር ከበርቴዎች ይበላሉ፤ ይሰግዱለታልም፤ ነፍሱን በሕይወት ማቈየት የማይችለው፣ ወደ ዐፈር ተመላሽ የሆነው ሁሉ በፊቱ ይንበረከካል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 መንግሥት ለጌታ ነውና፥ እርሱም አሕዛብን ይገዛል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ጌታ ሆይ! የተትረፈረፈ ሀብት ያላቸው ሁሉ ይሰግዱልሃል። ለሞትና ለመቃብር የተቃረቡትም መጥተው ይንበረከኩልሃል።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 22:29
20 Referencias Cruzadas  

ድኻውን ከዐፈር ያነሣል፤ ችግረኛውን ከዐመድ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤


የጢሮስ ሴት ልጅ እጅ መንሻ ይዛ ትመጣለች፤ ሀብታሞችም ደጅ ይጠኑሻል።


የሠባ ዐይናቸው ይጕረጠረጣል፤ ልባቸውም በከንቱ ሐሳብ ተሞልቶ ይፈስሳል።


የእግዚአብሔር ቍጣ በላያቸው ላይ መጣ፤ ከመካከላቸውም ብርቱ ነን ባዮችን ገደለ፤ የእስራኤልንም አበባ ወጣቶች ቀጠፈ።


ስለዚህ ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ በፈረጠሙ ጦረኞቹ ላይ የሚያከሳ በሽታ ይልካል፤ ከክብሩም በታች እንደ ነበልባል የሚንቦገቦግ እሳት ይለኰሳል።


ነገር ግን ሙታንህ ሕያዋን ይሆናሉ፤ በድናቸውም ይነሣል። እናንተ በዐፈር ውስጥ የምትኖሩ፣ ተነሡ፤ በደስታም ዘምሩ። ጠልህ እንደ ንጋት ጠል ነው፤ ምድር ሙታንን ትወልዳለች።


ወደ ታች ትወርጃለሽ፤ ከምድርም በታች ትናገሪያለሽ፤ ንግግርሽ ከትቢያ እየተጕተመተመ ይወጣል፤ ድምፅሽ እንደ መናፍስት ድምፅ ከመሬት ወደ ላይ ይመጣል፤ ንግግርሽ ከትቢያ ያንሾካሹካል።


ጕልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፤ ምላስም ሁሉ በእኔ ይምላል፤ ብዬ በራሴ ምያለሁ፤ የማይታጠፍ ቃል፣ ከአፌ በጽድቅ ወጥቷል።


የመንግሥታትን ወተት ትጠጪያለሽ፤ የነገሥታትንም ጡት ትጠቢያለሽ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር አዳኝሽ፣ ቤዛሽም እኔ የያዕቆብ ኀያል እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ።


“እስራኤል ሆይ፤ በእኔ ላይ ስለ ተነሣህ፣ ረዳትህንም ስለ ተቃወምህ ትጠፋለህ።


የዔሳውን ተራሮች ለመግዛት፣ ነጻ አውጪዎች ወደ ጽዮን ተራራ ይወጣሉ፤ መንግሥቱም የእግዚአብሔር ይሆናል።


በወልድ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት አለው፤ በወልድ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በላዩ ይሆናል እንጂ ሕይወትን አያይም።”


ይኸውም በሰማይና በምድር፣ ከምድርም በታች፣ ጕልበት ሁሉ ለኢየሱስ ስም ይንበረከክ ዘንድ፣


ሕዝቦች በብርሃኗ ይመላለሳሉ፤ የምድር ነገሥታትም ክብራቸውን ወደ እርሷ ያመጣሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos