Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 21:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ሕይወትን ለመነህ፤ ረዥም ዘመናትንም እስከ ዘላለም ሰጠኸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በበጎ በረከት ደርሰህለታልና፥ ከንጹሕ ወርቅ የተሠራ ዘውድን በራሱ ላይ አኖርህ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ሕይወትን እንድትሰጠው ለመነህ፤ አንተም ረጅም ዕድሜና ዘለዓለማዊ የሆነ ሕይወትን ሰጠኸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 አባ​ቶ​ቻ​ችን አን​ተን አመኑ፥ አመኑ፥ አን​ተም አዳ​ን​ሃ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 21:4
15 Referencias Cruzadas  

የደማቸውም ዕዳ ለዘላለም በኢዮአብና በዘሩ ራስ ላይ ይሁን። ነገር ግን በዳዊትና በዘሩ፣ በቤቱና በዙፋኑ ላይ የእግዚአብሔር ሰላም ለዘላለም ጸንቶ ይኑር።”


ንጉሥ ሰሎሞን ግን ይባረካል፤ የዳዊትም ዙፋን በእግዚአብሔር ፊት ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።”


ዮዳሄም የንጉሡን ልጅ አውጥቶ ዘውዱን ጫነለት፤ ኪዳኑንም ሰጠው፤ መንገሡን ዐወጁ፤ ቀብተውም አነገሡት። ከዚያም ሕዝቡ፣ “ንጉሡ ሺሕ ዓመት ይንገሥ” እያሉ በማጨብጨብ ደስታቸውን ከፍ ባለ ድምፅ ገለጹ።


አመሰግንህ ዘንድ በሕይወት ልኑር፤ ሕግህም ይርዳኝ።


ሕግህ ደስታዬ ነውና፣ በሕይወት እኖር ዘንድ ቸርነትህ ትምጣልኝ።


እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ተመልከት፤ ስማኝም። የሞት እንቅልፍ እንዳልተኛ ዐይኖቼን አብራ፤


ደግሞም በጽዮን ተራራ ላይ እንደሚወርድ፣ እንደ አርሞንዔም ጠል ነው፤ በዚያ እግዚአብሔር በረከቱን፣ ሕይወትንም እስከ ዘላለም አዝዟልና።


ስሙ ለዘላለም ጸንቶ ይኑር፤ ዝናው ፀሓይ የምትኖረውን ዘመን ያህል ይዝለቅ። ሕዝቦች ሁሉ በርሱ ይባረኩ፤ ሕዝቡ ሁሉ ቡሩክ ነህ ይበለው።


የዘር ሐረጉን ለዘላለም፣ ዙፋኑንም በሰማያት ዕድሜ ልክ አጸናለሁ።


ረዥም ዕድሜን አጠግበዋለሁ፤ ማዳኔንም አሳየዋለሁ።”


የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ የሚሠራው እርሱ ነው፤ ክብርን ይጐናጸፋል፤ በዙፋኑ ተቀምጦ ይገዛል፤ በዙፋኑም ላይ ካህን ይሆናል፤ በሁለቱም መካከል የሰላም ምክር ይኖራል።’


እኔ ሕያው ነኝ፤ ሞቼ ነበር፤ እነሆ፤ አሁን ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፤ የሞትና የሲኦል መክፈቻም በእጄ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos