Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 140:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እግዚአብሔር ለድኻ ፍትሕን እንደሚያስከብር፣ ለችግረኛውም ትክክለኛ ፍርድን እንደሚሰጥ ዐውቃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ተናጋሪ ሰው በምድር ውስጥ አይጸናም፥ ዓመፀኛን ሰው ክፋት ለጥፋት ይፈልገዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እግዚአብሔር ሆይ! ለድኾች እንደምትፈርድ፥ ለተጨቈኑትም መብታቸውን እንደምታስከብር ዐውቃለሁ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 140:12
16 Referencias Cruzadas  

ፍርዴም ጕዳዬም በአንተ እጅ ናቸውና፤ ቅን ፍርድ እየሰጠህ በዙፋንህ ላይ ተቀምጠሃል።


በማደሪያህ በሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውንና፤ ልመናቸውን ስማ፤ ፍረድላቸውም።


ጸሎትና ልመናቸውን በሰማይ ሆነህ ስማ፤ ፍትሕንም አጐናጽፋቸው።


ዐይነ ስውራን ያያሉ፤ ዐንካሶች ይራመዳሉ፤ ለምጻሞች ይነጻሉ፤ ደንቆሮዎች ይሰማሉ፤ ሙታን ይነሣሉ፤ ለድኾችም የምሥራች እየተሰበከ ነው፤


የድኾችንና የችግረኞችን ፍትሕ አላጓደለም፤ ስለዚህም ሁሉ መልካም ሆነለት። እኔን ማወቅ ማለት ይህ አይደለምን?” ይላል እግዚአብሔር።


እርሱ ወደ ችግረኞች ጸሎት ይመለከታል፤ ልመናቸውንም አይንቅም።


የሠራ አካላቴ እንዲህ ይልሃል፤ “እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ አንተ ማን አለ? ችግረኛውን ከርሱ ከሚበረቱ፣ ችግረኛውንና ድኻውን ከቀማኞች ታድናለህ።”


ነገር ግን ለድኾች በጽድቅ ይፈርዳል፤ ለምድር ምስኪኖችም ፍትሕን ይበይናል፤ በአፉ በትር ምድርን ይመታል፤ በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።


ድኾች በመሆናቸው ብቻ ድኾችን አትበዝብዛቸው፤ ችግረኛውንም በአደባባይ አታንገላታው፤


ለተቸገረው ሕዝብ ይሟገታል፤ የድኾችን ልጆች ያድናል፤ ጨቋኙንም ያደቅቀዋል።


እርሱ የተጨነቀውን ሰው ጭንቀት፣ አልናቀም፤ ቸልም አላለምና፤ ፊቱንም ከርሱ አልሰወረም፤ ነገር ግን ድረስልኝ ብሎ ሲጮኽ ሰማው።


ሸንጋዩን ከንፈር ሁሉ፣ ነገር የምታበዛውንም ምላስ እግዚአብሔር ያጥፋ!


እነዚህም፣ “በአንደበታችን እንረታለን፤ ከንፈራችን የእኛ ነው፤ ጌታችንስ ማነው?” የሚሉ ናቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios