Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 135:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እግዚአብሔር ታላቅ እንደ ሆነ፣ ጌታችንም ከአማልክት ሁሉ እንደሚበልጥ ዐውቃለሁና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ጌታ ታላቅ እንደሆነ፥ ጌታችንም ከአማልክት ሁሉ እንደሚበልጥ አውቄአለሁና።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እግዚአብሔር ከአማልክት ሁሉ የሚበልጥ ታላቅ አምላክ መሆኑን ዐውቃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ሰማ​ያ​ትን በጥ​በቡ የሠራ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 135:5
13 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ በምድር ሁሉ ላይ ልዑል ነህና፤ ከአማልክትም ሁሉ በላይ እጅግ ከፍ ያልህ ነህ።


እግዚአብሔር ታላቅ አምላክ ነውና፤ ከአማልክትም ሁሉ በላይ ታላቅ ንጉሥ ነው።


እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤ በአምላካችን ከተማ በተቀደሰው ተራራ ከፍ ያለ ምስጋና ይገባዋል።


አምላካችሁ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ፣ የጌቶች ጌታ ታላቅ አምላክ፣ ኀያልና የሚያስፈራ፣ አድልዎ የማያደርግ፣ መማለጃም የማይቀበል ነውና።


ስለዚህ እንደዚህ የሚያድን ሌላ አምላክ የለምና በሲድራቅ፣ በሚሳቅና በአብደናጎ አምላክ ላይ ማንኛውንም ቃል የሚናገሩ ሕዝቦችም ሆኑ ልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ሁሉ ይቈራረጣሉ፤ ቤቶቻቸውም የፍርስራሽ ክምር ይሆናሉ ብዬ አዝዣለሁ።”


ቅዱሱ፣ “ከማን ጋራ ታወዳድሩኛላችሁ? የሚስተካከለኝስ ማን አለ?” ይላል።


እርሱ ከምድር ክበብ በላይ በዙፋን ላይ ይቀመጣል፤ ሕዝቦቿም እንደ አንበጣ ናቸው። ሰማያትን እንደ ድባብ ይዘረጋቸዋል፤ እንደ መኖሪያ ድንኳንም ይተክላቸዋል።


በላይ በሰማያት ከእግዚአብሔር ጋራ ማን ሊስተካከል ይችላል? ከሰማያውያን ፍጥረታትስ መካከል ማን እግዚአብሔርን ይመስለዋል?


ጌታችን ታላቅ ነው፤ እጅግ ኀያልም ነው፤ ለጥበቡም ወሰን የለውም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios