Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 132:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 እነሆ፤ በኤፍራታ ሰማነው፤ በቂርያትይዓሪም አገኘነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እነሆ፥ በኤፍራታ ሰማነው፥ በጁኦሪም ምድር አገኘነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 በኤፍራታ ሆነን ስለ ቃል ኪዳኑ ታቦት ሰማን፤ በጁአሪም ምድር አገኘነው።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 132:6
7 Referencias Cruzadas  

ዳዊት በይሁዳ የቤተ ልሔሙ ሰው የኤፍራታዊው የእሴይ ልጅ ነበር። እሴይ ስምንት ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ በሳኦልም ዘመን ያረጀና ዕድሜው የገፋ ሰው ነበር።


የቂርያትይዓይሪም ሰዎችም መጥተው የእግዚአብሔርን ታቦት ይዘው ወጡ፤ ከዚያም በኰረብታው ላይ ወዳለው ወደ አሚናዳብ ቤት ወሰዱት። የእግዚአብሔርን ታቦት እንዲጠብቅም ልጁን አልዓዛርን ቀደሱት።


“አንቺ ግን፣ ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፤ ከይሁዳ ነገዶች መካከል ትንሿ ብትሆኚም፣ አመጣጡ ከጥንት፣ ከቀድሞ ዘመን የሆነ፣ የእስራኤል ገዥ፣ ከአንቺ ይወጣልኛል።”


የሰውየው ስም አሊሜሌክ፣ የሚስቱ ኑኃሚን፣ የሁለቱም ወንዶች ልጆቹ ስም መሐሎንና ኬሌዎን ነበር። እነርሱም የይሁዳ ቤተ ልሔም ኤፍራታውያን ሲሆኑ፣ ወደ ሞዓብ አገር ሄደው በዚያ ኖሩ።


ራሔልም ሞተች፤ ወደ ኤፍራታ በሚወስደው መንገድ በቤተ ልሔም ተቀበረች።


የእግዚአብሔርንም ታቦት በአዲስ ሠረገላ ላይ አኑረው፣ በኰረብታ ላይ ካለው ከአሚናዳብ ቤት አውጥተው አመጡ፤ ሠረገላውን ይነዱ የነበሩትም የአሚናዳብ ልጆች ዖዛና አሒዮ ሲሆኑ፣


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios