9 ልጆቹ ድኻ አደጎች ይሁኑ፤ ሚስቱም መበለት ትሁን።
9 ልጆቹም ያለ አባት ይቅሩ፥ ሚስቱም መበለት ትሁን።
9 ልጆቹ ያለ አባት ይቅሩ፤ ሚስቱም ባልዋ የሞተባት ሴት ትሁን።
ቍጣዬ ይነሣል፤ በሰይፍም እገድላችኋለሁ፤ ሚስቶቻችሁ መበለቶች፣ ልጆቻችሁም አባት የለሽ ይሆናሉ።
ስለዚህ ልጆቻቸውን ለራብ፣ ለሰይፍም ስለት አሳልፈህ ስጥ፤ ሚስቶቻቸው የወላድ መካን፣ መበለትም ይሁኑ፤ ወንዶቻቸው በሞት ይቀሠፉ፤ ጕልማሶቻቸው በጦር ሜዳ ለሰይፍ ይዳረጉ።
ወላጅ አልባና አባት የሌላቸው ሆንን፤ እናቶቻችን እንደ መበለቶች ሆኑ።