Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 109:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 መርገምን እንደ ልብስ ለበሳት፤ እርሷም እንደ ውሃ ወደ ውስጥ ሰውነቱ፣ እንደ ዘይትም ወደ ዐጥንቱ ዘለቀች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 መራገምን እንደ ልብስ ለበሳት፥ እንደ ውኃም ወደ አንጀቱ፥ እንደ ቅባትም ወደ አጥንቱ ገባች።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 መራገም ልብስ የመልበስ ያኽል ይቀልለው ነበር፤ ስለዚህ የራሱ ርግማን እንደ ውሃ ወደ ሰውነቱ ገብቶ ያረስርሰው፤ እንደ ዘይትም ወደ አጥንቱ ዘልቆ ይግባ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 109:18
14 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ ትዕቢት የዐንገት ጌጣቸው ነው፤ ዐመፅንም እንደ ልብስ ተጐናጽፈዋል።


ይህን ርግማን የሚያመጣ ውሃ በጠጣሽ ጊዜም ሆድሽን ያሳብጠው፤ ጭንሽን ያስልለው።” “ ‘ሴትዮዋም፣ “አሜን፤ አሜን” ትበል።


እንግዲህ የተቀደሳችሁና የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ምርጦች እንደ መሆናችሁ ርኅራኄን፣ ቸርነትን፣ ትሕትናን፣ ጨዋነትንና ትዕግሥትን ልበሱ፤


ጕልማሶች ሆይ፤ እናንተም እንዲሁ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርስ በመከባበር ትሕትናን ልበሱ፤ ምክንያቱም፣ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።”


አሁን ግን ቍጣን፣ ንዴትን፣ ክፋትን፣ ስድብንና አሳፋሪ ንግግርን የመሳሰሉትንም ሁሉ አስወግዱ፤


ይሁዳ ወደ ገዛ ራሱ ስፍራ ትቶት በሄደው በዚህ አገልግሎትና በሐዋርያዊነት ቦታ ላይ ሹመው።”


ይህ ሰው ስለ ክፉ ሥራው በተከፈለው ዋጋ መሬት ገዛ፤ በዚያም በግንባሩ ተደፍቶ ሰውነቱ እመካከሉ ላይ ፈነዳ፤ ሆድ ዕቃውም ተዘረገፈ።


የሰው ልጅ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈው ይሄዳል፤ ነገር ግን የሰውን ልጅ አሳልፎ ለሚሰጠው ለዚያ ሰው ወዮለት! ያ ሰው ሳይወለድ ቢቀር ይሻለው ነበር።”


ጽድቅን እንደ ልብስ ለበስሁ፤ ፍትሕም መጐናጸፊያዬና ጥምጥሜ ነበር።


ራሷን በማጕደፍ ለባሏ ባትታመን፣ ርግማን የሚያመጣውን ውሃ እንድትጠጣ ሲደረግ ውሃው ወደ ሰውነቷ ገብቶ ክፉ ሥቃይ ያመጣባታል፤ ሆዷ ያብጣል፤ ጭኗ ይሰልላል፤ በሕዝቦቿም ዘንድ የተረገመች ትሆናለች።


ገላውን እንደሚሸፍንበት ልብስ፣ ዘወትር እንደሚታጠቀውም መቀነት ትሁነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios