Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 10:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ክፉ ሰው በእግዚአብሔር ላይ ለምን ክፉ ይናገራል? በልቡስ፣ “ስለ ሥራዬ አይጠይቀኝም” ለምን ይላል?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ክፉ ስለምን እግዚአብሔርን ናቀ? በልቡም፦ “ፈልጎ አያገኘኝም” ይላልና።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ክፉ ሰዎች ለምን አያከብሩህም? ለምንስ በልባቸው “እግዚአብሔር አይቀጣንም” ይላሉ?

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 10:13
13 Referencias Cruzadas  

“እናንተን የሚሰማ እኔን ይሰማል፤ እናንተን የማይቀበል እኔን አይቀበልም፤ እኔንም የማይቀበል የላከኝን አይቀበልም።”


እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላት እንዴት እንደሚያሾፍ፣ ሞኝ ሕዝብም ስምህን እንዴት እንዳቃለለ ዐስብ።


አምላክ ሆይ፤ ጠላት የሚያሾፈው እስከ መቼ ነው? ባላንጣስ ለዘላለም በስምህ ያላግጣልን?


ንጉሥ ኢዮአስ የዘካርያስ አባት ዮዳሄ ያደረገለትን ቸርነት አላሰበም፤ በዚህ ፈንታ ልጁን ገደለው፤ በሚሞትበትም ጊዜ፣ “እግዚአብሔር ይየው፤ እርሱው ይበቀልህ” አለ።


ነገር ግን በአፍንጫችሁ እስኪወጣና እስኪያንገፈግፋችሁ ድረስ ወር ሙሉ ትበሉታላችሁ፤ በመካከላችሁ ያለውን እግዚአብሔርን ንቃችሁ በፊቱ፣ “ለምን ከግብጽ ወጣን?” ብላችሁ አልቅሳችኋልና።’ ”


ሰውን የገደለ ሁሉ ስለ ሟቹ ደም ተጠያቂ ነው፤ የሟቹን ሰው ደም ከገዳዩ፣ ከእንስሳም ይሁን ከሰው እሻለሁ።


እንግዲህ ይህን ምክር ንቆ የማይቀበል፣ የናቀው ቅዱስ መንፈሱን የሰጣችሁን እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን አይደለም።


ሮቤልም መልሶ፣ “በዚህ ልጅ ላይ፣ ‘ክፉ ነገር አታድርጉ’ ብዬ አልነበረምን? እናንተ ግን አልሰማችሁኝም፤ ስለዚህም ደሙ ከእጃችን ይፈለጋል” አላቸው።


የእነዚህን ሕዝቦች አማልክት ለማምለክ ልቡን ከአምላካችን ከእግዚአብሔር የሚመልስ ወንድም ሆነ ሴት ጐሣም ሆነ ነገድ ዛሬ ከመካከላችሁ አለመገኘቱን አረጋግጡ፤ ከመካከልህ እንዲህ ያለውን መራራ መርዝ የሚያወጣ ሥር እንዳይኖር ተጠንቀቁ።


የሟቾች ጣር ጩኸት ከከተማዋ ይሰማል፤ የቈሰሉት ሰዎች ነፍስ ለርዳታ ይጮኻል፤ እግዚአብሔር ግን ተጠያቂዎቹን ዝም ብሏል።


ያለ ሥጋት እንዲኖሩ ትቷቸው ይሆናል፤ ዐይኖቹ ግን በመንገዳቸው ላይ ናቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios