Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 24:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በዕውቀትም ውድና ውብ በሆነ ንብረት፣ ክፍሎቹ ይሞላሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በእውቀት የቤት ክፍሎች በከበረውና ባማረው ሀብት ሁሉ ይሞላሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ዕውቀት ሲኖር ቤት በከበሩና በሚያምሩ ዕቃዎች ይሞላል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በዕውቀት ከከበረውና ካማረው ሀብት ሁሉ ጓዳዎች ይሞላሉ።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 24:4
16 Referencias Cruzadas  

በጠቢብ ቤት ምርጥ ምግብና ዘይት ተከማችቶ ይገኛል፤ ሞኝ ሰው ግን ያለ የሌለውን ያሟጥጣል።


የጻድቃን ቤት በብዙ ሀብት የተሞላ ነው፤ የክፉዎች ገቢ ግን መከራን ታመጣባቸዋለች።


ወርቁም አለ፤ ቀዩም ዕንቍ ተትረፍርፏል፤ ዕውቀት የሚናገሩ ከንፈሮች ግን ብርቅ ጌጦች ናቸው።


ለሚወድዱኝ ብልጽግና እሰጣለሁ፤ ግምጃ ቤታቸውንም እሞላለሁ።


እርሱም፣ “ስለዚህም የመንግሥተ ሰማይን ምስጢር የተረዳ ማንኛውም የኦሪት ሕግ መምህር፣ ከከበረ ሀብቱ ክምችት አዲሱንም አሮጌውንም የሚያወጣ ባለንብረት ይመስላል” አላቸው።


የእስራኤል ሕዝብና ሌዋውያኑ ጭምር፣ ከእህሉ፣ ከአዲሱ ወይን ጠጅና ከዘይቱ ያዋጡትን፣ የመቅደሱ ዕቃዎች ወደሚቀመጡባቸው፣ አገልጋይ ካህናት፣ በር ጠባቂዎቹና መዘምራኑ ወደሚያርፉባቸው ዕቃ ቤቶች ያምጡ። “እኛም የአምላካችንን ቤት ቸል አንልም።”


ጠቢብ ሰው ታላቅ ኀይል አለው፤ ዕውቀት ያለውም ሰው ብርታትን ይጨምራል፤


በድንጋይ ውስጥ መተላለፊያ ያበጃል፤ ዐይኖቹም የከበሩ ነገሮችን ሁሉ ያያሉ።


ሀብትና ክብር፣ ዘላቂ ብልጽግናና ስኬት በእኔ ዘንድ አሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios