Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 6:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ከዚያም ካህኑ የሚወዘወዝ መሥዋዕት በማድረግ በእግዚአብሔር ፊት ይወዘውዛቸዋል፤ እነዚህም የተቀደሱ ናቸው። ከተወዘወዘው ፍርምባና ከቀረበው ወርች ጋራ የተቀደሱ የካህኑ ድርሻ ይሆናሉ። ከዚህ በኋላ ናዝራዊው የወይን ጠጅ መጠጣት ይችላል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ካህኑም እነዚህን ለመወዝወዝ ቁርባን በጌታ ፊት ይወዘውዛቸዋል፤ ይህም ከሚወዘወዘው ፍርምባና ከሚቀርበው ወርች ጋር ለካህኑ የተቀደሰ ድርሻው ነው። ከዚያም በኋላ ናዝራዊው ወይን ሊጠጣ ይችላል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ከዚህም በኋላ ካህኑ ይህን ሁሉ ወስዶ ለእግዚአብሔር የሚወዘወዝ ልዩ መባ አድርጎ ያቀርበዋል፤ ይህም ሁሉ የካህኑ ድርሻ ሆኖ ከሚነሣው ከአውራው በግ ፍርንባና ወርች ጋር ለካህኑ የተቀደሰ ድርሻ ይሆናል፤ ናዝራዊው የወይን ጠጅ መጠጣት የሚፈቀድለትም ከዚያን በኋላ ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ካህ​ኑም እነ​ዚ​ህን ሁሉ ቍር​ባን አድ​ርጎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቀ​ር​ባል፤ ይህም የቍ​ር​ባን ፍር​ም​ባና የመ​ባው ወርች ለካ​ህኑ የተ​ቀ​ደሰ ነው፤ ከዚ​ያም በኋላ ባለ​ስ​እ​ለቱ ወይን ይጠ​ጣል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ካህኑም እነዚህን ለመወዝወዝ ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ይወዘውዛቸዋል፤ ይህም ከሚወዘወዘው ፍርምባና ከሚነሣው ወርች ጋር ለካህኑ የተቀደሰ ነው። ከዚያም በኋላ ናዝራዊው ወይን ይጠጣ ዘንድ ይችላል።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 6:20
24 Referencias Cruzadas  

ሂድ፤ ምግብህን በደስታ ብላ፤ ወይንህንም ልብህ ደስ ብሎት ጠጣ፤ ባደረግኸው ነገር አምላክ ደስ ብሎታልና።


የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በዚህ ተራራ ላይ፣ ለሕዝብ ሁሉ ታላቅ የምግብ ግብዣ፣ የበሰለ የወይን ጠጅ ድግስ፣ ማለፊያ ጮማና ምርጥ የወይን ጠጅ ያዘጋጃል።


እግዚአብሔር የተቤዣቸው ይመለሳሉ፤ በዝማሬ ወደ ጽዮን ይገባሉ፤ ዘላለማዊ ደስታን ይጐናጸፋሉ፤ ደስታና ሐሤት ይቀድማሉ፤ ሐዘንና ትካዜም ይሸሻሉ።


የቀረበውን ወርችና የተወዘወዘውን ፍርምባ በእግዚአብሔር ፊት የመወዝወዝ መሥዋዕት ሆኖ በእሳት ከቀረበው ሥብ ጋራ ይምጣ። ይህም እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ለአንተና ለልጆችህ ለዘላለም የተመደበ ድርሻ ይሆናል።”


ነዶው ተቀባይነት እንዲያገኝላችሁም በእግዚአብሔር ፊት ይወዝውዘው፤ ካህኑ ነዶውን የሚወዘውዘው በሰንበት ቀን ማግስት ነው።


በእሳት ለእግዚአብሔር የሚቀርበውን መሥዋዕት በራሱ እጅ ያቅርበው፤ ሥቡን ከፍርምባው ጋራ ያቅርብ፤ ፍርምባውን መሥዋዕት አድርጎ በእግዚአብሔር ፊት ይወዝውዘው።


ካህኑ ሥቡን በመሠዊያው ላይ ያቃጥል፤ ፍርምባው ግን ለአሮንና ለልጆቹ ይሰጥ።


የኅብረት መሥዋዕታችሁን የቀኝ ወርች ለካህኑ የተለየ አድርጋችሁ ስጡት።


ከእስራኤላውያን የኅብረት መሥዋዕት ላይ የተወዘወዘውን ፍርምባና የቀረበውን ወርች ወስጃለሁ፤ ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹም ከእስራኤላውያን የሚያገኙት መደበኛ ድርሻቸው እንዲሆን ሰጥቻቸዋለሁ።’ ”


አሮንም ፍርምባዎቹንና የቀኝ ወርቹንም ሙሴ ባዘዘው መሠረት፣ የመወዝወዝ መሥዋዕት አድርጎ በእግዚአብሔር ፊት ወዘወዘው።


ኤፍሬማውያን እንደ ኀያላን ሰዎች ይሆናሉ፤ ልባቸውም የወይን ጠጅ እንደ ጠጣ ሰው ሐሤት ያደርጋል። ልጆቻቸው ያዩታል፤ ደስተኛም ይሆናሉ፤ ልባቸውም በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል።


የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ይከልላቸዋል፤ ጠላቶቻቸውን ይደመስሳሉ፤ በድንጋይ ወንጭፍም ያሸንፋሉ፤ ይጠጣሉ፤ በወይን ጠጅ እንደ ሰከረ ሰው ይጮኻሉ፤ የመሠዊያውን ማእዘኖች ለመርጨት፣ እንደ ተዘጋጀ ዕቃ፣ እነርሱም እንደዚሁ ተሞልተዋል።


እንዴት ውብና አስደናቂ ይሆናሉ፤ እህል ጕልማሶችን፣ አዲስ የወይን ጠጅም ቈነጃጅትን ያሳምራል።


የሚወዘወዘው ቍርባን ፍርምባና የቀኙ ወርች የአንተ እንደ ሆነ ሁሉ የእነዚህም ሥጋ የአንተ ይሆናል።


ካህኑ ለቅናት የቀረበውን የእህል ቍርባን ይቀበላት፤ በእግዚአብሔር ፊት ወዝውዞ ወደ መሠዊያው ያቅርበው።


“ ‘ስእለቱን ለመፈጸም ለእግዚአብሔር ለሚሳል ናዝራዊ ሕጉ ይኸው ነው፤ ሊቀርብ ከሚችለው በላይ ለእግዚአብሔር ለመስጠት ቃል ለሚገባው ነገር እንደ ናዝራዊነቱ በተሳለው መሠረት መሆን አለበት። በናዝራዊነት ሕግ መሠረት የተሳለውን ስእለት መፈጸም ይገባዋል።’ ”


እላችኋለሁ፤ በአባቴ መንግሥት ከእናንተ ጋራ በአዲስ መልክ እስከምጠጣበት እስከዚያ ቀን ድረስ፣ ከአሁን ጀምሮ ከዚህ የወይን ፍሬ አልጠጣም።”


እውነት እላችኋለሁ፤ በእግዚአብሔር መንግሥት አዲሱን የወይን ፍሬ እስከምጠጣበት እስከዚያች ቀን ድረስ ዳግም ከወይን ፍሬ አልጠጣም።”


ኢየሱስም ኮምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ፣ “ተፈጸመ” አለ፤ ራሱን አዘንብሎ፣ መንፈሱን አሳልፎ ሰጠ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos