Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 31:54 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

54 ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ወርቁን ከሻለቆቹና ከመቶ አለቆቹ ተቀብለው በእግዚአብሔር ፊት ለእስራኤላውያን መታሰቢያ እንዲሆን ወደ መገናኛው ድንኳን አመጡት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

54 ሙሴና ካህኑ አልዓዛርም ወርቁን ከሻለቆችና ከመቶ አለቆች ወስደው በጌታ ፊት ለእስራኤል ልጆች መታሰቢያ ወደ መገናኛው ድንኳን አገቡት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

54 ስለዚህ ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ወርቁን ከሺህ አለቆችና ከመቶ አለቆች ተቀብለው ለእስራኤላውያን መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ወደ መገናኛው ድንኳን አመጡት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

54 ሙሴና ካህኑ አል​ዓ​ዛ​ርም ወር​ቁን ከሻ​ለ​ቆ​ችና ከመቶ አለ​ቆች ወሰዱ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መታ​ሰ​ቢያ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን አገ​ቡት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

54 ሙሴና ካህኑ አልዓዛርም ወርቁን ከሻለቆችና ከመቶ አለቆች ወስደው በእግዚአብሔር ፊት ለእስራኤል ልጆች መታሰቢያ ወደ መገናኛው ድንኳን አገቡት።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 31:54
12 Referencias Cruzadas  

የማስተስረያውን ገንዘብ ከእስራኤላውያን ተቀብለህ ለመገናኛው ድንኳን አገልግሎት አውለው፤ ለሕይወታችሁ ማስተስረያ በማድረግ በእግዚአብሔር ፊት የእስራኤላውያን ማስተስረያ ይሆናል።”


አክሊሉም ለሔሌምና ለጦብያ፣ ለዮዳኤና ለሶፎንያስ ልጅ ለሔን በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ መታሰቢያ ይሆናል።


ቆርኔሌዎስም በድንጋጤ ትኵር ብሎ እያየው፣ “ጌታ ሆይ፤ ምንድን ነው?” አለው። መልአኩም እንዲህ አለው፤ “ጸሎትህና ምጽዋትህ ለመታሰቢያነት ወደ እግዚአብሔር ፊት ዐርጎልሃል።


እንጀራንም አንሥቶ አመሰገነ፤ ቈርሶም ሰጣቸውና፣ “ይህ ስለ እናንተ የሚሰጥ ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” አለ።


የበጎነትህን ብዛት በደስታ ያወሳሉ፤ ስለ ጽድቅህም በእልልታ ይዘምራሉ።


ለእኛ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ለእኛ ሳይሆን፣ ስለ ምሕረትህና ስለ እውነትህ፣ ለስምህ ክብርን ስጥ።


ስለዚህ እግዚአብሔር ሆይ፤ በአሕዛብ መካከል አመሰግንሃለሁ፤ ስምህንም በመዝሙር እወድሳለሁ።


የዮርዳኖስ ወንዝ በእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት መቆሙን፣ እንዲሁም ታቦቱ ዮርዳኖስን በሚሻገርበት ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ ውሃ መቆሙን፣ እነዚህ ድንጋዮች ለእስራኤል ሕዝብ የዘላለም መታሰቢያ መሆናቸውን ንገሯቸው።”


ይህን ያደረገውም፣ እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ባዘዘው መሠረት ነው፤ ይህም ከአሮን ዘር በቀር ማንም ሰው በእግዚአብሔር ፊት ቀርቦ ዕጣን እንዳያጥን አለዚያ ግን፣ እንደ ቆሬና እንደ ተከታዮቹ እንደሚሆን ለእስራኤላውያን የተሰጠ ማስጠንቀቂያ ነበር።


ለእስራኤል ልጆች መታሰቢያ ድንጋዮች ይሆኑ ዘንድ በኤፉዱ ትከሻ ላይ ካሉት ንጣዮች ጋራ አያይዛቸው፤ በእግዚአብሔር ፊት መታሰቢያ እንዲሆኑ አሮን ስሞቹን በትከሻው ላይ ይሸከማቸው።


የአቢሱ ልጅ፣ የፊንሐስ ልጅ፣ የአልዓዛር ልጅ፣ የታላቁ ካህን የአሮን ልጅ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios