Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 3:40 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “በኵር ሆነው የተወለዱትን፣ አንድ ወርና ከዚያ በላይ የሆናቸውን እስራኤላውያን ወንዶች ሁሉ ቍጠር፤ ዝርዝራቸውንም ያዝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የእስራኤልን ልጆች የወንድ በኩር ሁሉ ቁጠር፤ ዕድሜቸው አንድ ወር የሞላቸውንና ከዚያም በላይ ያሉትን በየስማቸው ቈጥረህ ቁጥሩን ውሰድ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “በኲር ሆነው የተወለዱትን የእስራኤላውያን ወንዶች ልጆች ዕድሜአቸው አንድ ወርና ከዚያም በላይ የሆነውን ቈጥረህ በየስማቸው መዝግብ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ወን​ዱን በኵር ሁሉ ከአ​ንድ ወር ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያሉ​ትን ቍጠር፤ ቍጥ​ራ​ቸ​ው​ንም በየ​ስ​ማ​ቸው ውሰድ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 እግዚአብሔርም ሙሴን፦ የእስራኤልን ልጆች ወንዱን በኵር ሁሉ ቍጠር፤ ከአንድ ወር ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉትን የስማቸውን ቍጥር ውሰድ፤

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 3:40
13 Referencias Cruzadas  

“ሌዋውያንን በየቤታቸውና በየጐሣቸው ቍጠር፤ የምትቈጥረውም አንድ ወርና ከዚያ በላይ የሆነውን ወንድ ሁሉ ነው” አለው።


እነዚህ ራሳቸውን በሴቶች ያላረከሱት ናቸው፤ ራሳቸውን በንጽሕና ጠብቀዋልና። በጉ ወደሚሄድበት ሁሉ ይከተሉታል፤ ለእግዚአብሔርና ለበጉ በኵራት እንዲሆኑ ከሰዎች መካከል የተዋጁ ናቸው።


ድል የሚነሣም እንደ እነርሱ ነጭ ልብስ ይለብሳል፤ እኔም በአባቴና በመላእክቱ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ ስሙንም ከሕይወት መጽሐፍ አልደመስስም።


ስማቸው በሰማይ ወደ ተጻፈው ወደ በኵራት ማኅበር ቀርባችኋል፤ የሁሉ ዳኛ ወደ ሆነው ወደ እግዚአብሔር፣ ፍጹምነትን ወዳገኙት ወደ ጻድቃን መንፈሶች፣


ይሁን እንጂ፣ “ጌታ የርሱ የሆኑትን ያውቃል” ደግሞም፣ “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከክፋት ይራቅ” የሚል ማኅተም ያለበት የማይነቃነቅ የእግዚአብሔር መሠረት ቆሟል።


አዎን፤ አንተ ታማኝ ባልደረባዬ ሆይ፤ ወንጌልን በማሠራጨት ረገድ ከእኔና ከቀሌምንጦስ ጋራ እንዲሁም ስማቸው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት ከሌሎች የሥራ ጓደኞቼ ጋራ የተጋደሉትን እነዚህን ሴቶች እንድትረዳቸው እለምንሃለሁ።


ይሁን እንጂ መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚያ ደስ አይበላችሁ፤ ስማችሁ ግን በሰማይ ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ።”


በጽዮን የቀሩት፣ በኢየሩሳሌምም የተረፉት፣ በኢየሩሳሌም በሕይወት ከተመዘገቡት ሁሉ ጋራ ቅዱሳን ተብለው ይጠራሉ።


እግዚአብሔር ሕዝቡን ሲመዘግብ፣ “ይህ ሰው የተወለደው በዚያ ነው” ብሎ ይጽፋል። ሴላ


“በእስራኤላውያን በኵሮች ምትክ ሌዋውያኑን፣ በከብቶቻቸውም ምትክ የሌዋውያኑን ከብቶች ውሰድ፤ ሌዋውያኑም የእኔ ይሁኑ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


“እነሆ፤ በኵር ሆኖ በሚወለደው ሁሉ ምትክ ሌዋውያኑን ከእስራኤላውያን ወስጃለሁ፤ ስለዚህ ሌዋውያን የእኔ ናቸው፤


በኵር በሆኑት በእስራኤላውያን ልጆች ሁሉ ምትክ ሌዋውያንን እንዲሁም በኵር በሆኑት በእስራኤላውያን ከብቶች ሁሉ ምትክ የሌዋውያንን ከብቶች ለእኔ አድርጋቸው፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios