Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 27:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ ቀረቡ፤ በሙሴ፣ በካህኑ በአልዓዛር፣ በመሪዎችና በመላው ማኅበርም ፊት ቆመው እንዲህ አሉ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በመገናኛውም ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በሙሴና በካህኑ በአልዓዛር በአለቆቹም በማኅበሩም ሁሉ ፊት ቆመው እንዲህ አሉ፦

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እነርሱም በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ሄደው መላው ማኅበርና የሕዝቡ መሪዎች ባሉበት በሙሴና በአልዓዛር ፊት ቆመው እንዲህ አሉ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 በም​ስ​ክ​ሩም ድን​ኳን ደጃፍ አጠ​ገብ በሙ​ሴና በካ​ህኑ በአ​ል​ዓ​ዛር፥ በአ​ለ​ቆ​ቹም፥ በማ​ኅ​በ​ሩም ሁሉ ፊት ቆመው እን​ዲህ አሉ፦

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በመገናኛውም ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በሙሴና በካህኑ በአልዓዛር በአለቆቹም በማኅበሩም ሁሉ ፊት ቆመው፦

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 27:2
10 Referencias Cruzadas  

አንዳንዶቹ ግን የሰው ሬሳ በመንካታቸው በሥርዐቱ መሠረት ረክሰው ስለ ነበር በዚያ ዕለት የፋሲካን በዓል ማክበር አልቻሉም፤ ስለዚህም በዚያ ዕለት ወደ ሙሴና ወደ አሮን መጥተው፣


የምናሴ ልጅ፣ የማኪር ልጅ፣ የገለዓድ ልጅ፣ የአፌር ልጅ፣ የሰለጰዓድ ሴት ልጆች ከዮሴፍ ልጅ ከምናሴ ጐሣዎች ነበሩ፤ ስማቸውም ማህለህ፣ ኑዓ፣ ዔግላ፣ ሚልካና ቲርጻ ይባላል። እነርሱም፣


“አባታችን በምድረ በዳ ሞተ፤ ተባብረው በእግዚአብሔር ላይ ካመፁት ከቆሬ ተከታዮች ጋራ አልነበረም፤ የሞተው ግን በራሱ ኀጢአት ሲሆን፣ ወንዶች ልጆችም አልነበሩትም።


እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ሆኖ በኡሪም በመጠየቅ ውሳኔ በሚያስገኝለት በካህኑ በአልዓዛር ፊት ይቆማል፤ እርሱም ሆነ መላው የእስራኤል ማኅበረ ሰብ በአልዓዛር ትእዛዝ ይወጣሉ፤ በርሱም ቃል ይገባሉ።”


ከዮሴፍ ዝርያ ጐሣዎች የሆኑ የምናሴ ልጅ፣ የማኪር ልጅ፣ የገለዓድ ጐሣ የቤተ ሰብ አለቆች ወደ ሙሴና የእስራኤላውያን ቤተ ሰቦች አለቆች ወደሆኑት መሪዎች ቀርበው ተናገሩ፤


የአቢሱ ልጅ፣ የፊንሐስ ልጅ፣ የአልዓዛር ልጅ፣ የታላቁ ካህን የአሮን ልጅ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios