Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 27:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 “ሥጋ ለባሽ ሁሉ መንፈስ አምላክ የሆነ ጌታ እግዚአብሔር በዚህ ማኅበረ ሰብ ላይ ሰው ይሹም፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 የሥጋ ለባሽ ሁሉ መንፈስ አምላክ የሆነ ጌታ በማኅበሩ ላይ አንድ ሰው ይሹም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16-17 “ለሰው ሁሉ ሕይወትን የምትሰጥ፥ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ ሕዝብህ እረኛ እንደሌለው የበግ መንጋ እንዳይሆን፥ ሕዝብህን የሚመራ አንድ ሰው ምረጥ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 “የሥ​ጋና የነ​ፍስ ሁሉ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ሕዝብ ላይ የሚ​ሆ​ነ​ውን ሰው ይሹም፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16-17 የእግዚአብሔር ማኅበር እረኛ እንደሌለው መንጋ እንዳይሆን፥ በፊታቸው የሚወጣውን በፊታቸውም የሚገባውን የሚያስወጣቸውንም የሚያስገባቸውንም ሰው የሥጋ ሁሉ መንፈስ አምላክ እግዚአብሔር በማኅበሩ ላይ ይሹመው።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 27:16
20 Referencias Cruzadas  

ሙሴና አሮን ግን በግንባራቸው ተደፍተው፣ “የሥጋ ለባሽ ሁሉ መንፈስ አምላክ የሆንህ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንድ ሰው ኀጢአት በሠራ በመላው ማኅበር ላይ ትቈጣለህን?” ሲሉ ጮኹ።


ከዚህም በላይ፣ እኛ ሁላችን የሚቀጡን ምድራዊ አባቶች ነበሩን፤ እናከብራቸውም ነበር። ታዲያ ለመናፍስት አባት እንዴት አብልጠን በመገዛት በሕይወት አንኖርም!


እንደ ልቤም የሆኑ፣ በዕውቀትና በማስተዋል የሚመሯችሁን እረኞች እሰጣችኋለሁ።


ለራሳችሁና መንፈስ ቅዱስ ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ በላዩ ለሾማችሁ መንጋ ሁሉ ተጠንቀቁ፤ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ።


“መልካም እረኛ እኔ ነኝ፤ መልካም እረኛ ሕይወቱን ስለ በጎቹ አሳልፎ ይሰጣል፤


ስለዚህ የመከሩ ጌታ፣ ሠራተኞችን ወደ መከሩ እንዲልክ ለምኑት።”


“ ‘ባሪያዬ ዳዊት በላያቸው ይነግሣል፤ ሁሉም አንድ እረኛ ይኖራቸዋል፤ ሕጌን ይከተላሉ፤ ሥርዐቴንም በጥንቃቄ ይጠብቃሉ።


በእነርሱ ላይ አንድ እረኛ፣ ባሪያዬን ዳዊትን አቆማለሁ፤ እርሱም ያሰማራቸዋል፤ እረኛቸውም ይሆናል።


አሁንም የጠየቃችሁትና የመረጣችሁት ንጉሥ ይኸው፤ እነሆ፣ እግዚአብሔር በላያችሁ ንጉሥ አንግሧል።


እግዚአብሔር ሙሴን፣ “እነሆ የምትሞትበት ቀን ቀርቧል፤ ትእዛዝ እንድሰጠው ኢያሱን ጥራውና ወደ መገናኛው ድንኳን ቅረቡ።” ሙሴና ኢያሱም ሄዱ፤ ወደ መገናኛው ድንኳንም ቀረቡ።


እነሆ፣ እግዚአብሔር ለአባቴ ለዳዊት፣ ‘ለስሜ ቤተ መቅደስ የሚሠራልኝ ከአንተ ቀጥሎ በዙፋንህ የማስቀምጠው ልጅህ ነው’ ብሎ እንደ ነገረው፣ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ስም ቤተ መቅደስ ለመሥራት ዐስቤአለሁ።


ሙሴ እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤


እያንዳንዱ የጦር መሣሪያውን በእጁ ይዞ በንጉሡ ዙሪያ ሁኑ፤ የሚቀርባችሁ ማንም ሰው ቢኖር ግን ይገደል። ንጉሡ በሚወጣበትም ሆነ በሚገባበት ጊዜ ሁሉ ዐብራችሁት ሁኑ።”


ዐፈር ወደ መጣበት መሬት ሳይመለስ፣ መንፈስም ወደ ሰጠው ወደ አምላክ ሳይመለስ፣ ፈጣሪህን ዐስብ።


“እነሆ፤ እኔ የሰው ልጆች ሁሉ አምላክ እግዚአብሔር ነኝ፤ በውኑ የሚያቅተኝ ነገር አለን?


ንጉሥ ሴዴቅያስ፣ “ለኤርምያስ፣ እስትንፋስ የሰጠ ሕያው እግዚአብሔርን! በርግጥ አልገድልህም፤ ሕይወትህንም ለሚሿት አሳልፌ አልሰጥም” ብሎ በምስጢር ማለለት።


እነሆ ነፍስ ሁሉ የእኔ ናት፤ የአባት ነፍስ የእኔ እንደ ሆነች ሁሉ የልጁም ነፍስ የእኔ ናት፤ ኀጢአት የምትሠራ ነፍስ እርሷ ትሞታለች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios