Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 23:26 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 በለዓምም፣ “እግዚአብሔር የሚለኝን ሁሉ ማድረግ እንዳለብኝ አልነገርሁህምን?” ሲል መለሰለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 በለዓምም መልሶ ባላቅን፦ “ ‘ጌታ የተናገረውን ሁሉ አደርጋለሁ’ ብዬ ነግሬህ አልነበረምን?” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 በለዓምም “እኔ እግዚአብሔር የነገረኝን ብቻ እንደማደርግ ቀደም ብዬ አስታውቄህ አልነበረምን?” አለው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 በለ​ዓ​ምም መልሶ ባላ​ቅን አለው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረ​ኝን ቃል ሁሉ አደ​ር​ጋ​ለሁ ብዬ አል​ተ​ና​ገ​ር​ሁ​ህ​ምን?”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 በለዓምም መልሶ ባላቅን፦ እግዚአብሔር የተናገረውን ሁሉ አደርጋለሁ ብዬ አልተናገርሁህምን? አለው።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 23:26
12 Referencias Cruzadas  

ሚክያስ ግን፣ “ሕያው እግዚአብሔርን! እግዚአብሔር የነገረኝን ብቻ እነግረዋለሁ” አለ።


ሚክያስ ግን፣ “ሕያው እግዚአብሔርን! አምላኬ የሚለውን ብቻ እነግረዋለሁ” አለ።


በለዓም ግን እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “ሌላው ይቅርና ባላቅ በብርና በወርቅ የተሞላ ቤተ መንግሥቱን ቢሰጠኝ እንኳ፣ የአምላኬን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመጣስ ከዚያ ያለፈ ወይም ያነሰ ማንኛውንም ነገር ማድረግ አልችልም።


በለዓምም፣ “ይኸው አሁን መጥቻለሁ፤ ግን እንዲያው ማንኛውንም ነገር መናገር እችላለሁን? እኔ መናገር የሚገባኝ እግዚአብሔር በአፌ ያስቀመጠውን ብቻ ነው” ብሎ መለሰለት።


እርሱም ተመልሶ ሲሄድ ባላቅን ከመላው የሞዓብ አለቆች ጋራ በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ አገኘው፤ ባላቅም፣ “እግዚአብሔር ምን አለ?” ሲል ጠየቀው።


በዚህ ጊዜ ባላቅ በለዓምን፣ “እንግዲያውስ ፈጽሞ አትርገማቸው፤ ፈጽሞም አትመርቃቸው!” አለው።


ከዚህ በኋላ ባላቅ በለዓምን፣ “በል እንግዲያው ወደ ሌላ ቦታ ልውሰድህ፤ ከዚያ ሆነህ እንድትረግምልኝ ምናልባት እግዚአብሔር ይፈቅድልህ ይሆናል” አለው።


ከዚያም በለዓም ባላቅን፣ “እኔ ወደዚያ ስሄድ፣ አንተ እዚሁ መሥዋዕትህ አጠገብ ቈይ፤ ምናልባትም እግዚአብሔር ሊገናኘኝ ይመጣ ይሆናል፤ የሚገልጥልኝንም ሁሉ እነግርሃለሁ” አለው። ከዚያም በለዓም ወደ አንድ ገላጣ ኰረብታ ሄደ።


ጴጥሮስና ሌሎች ሐዋርያትም መልሰው እንዲህ አሉ፤ “ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል!


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos