Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሚክያስ 6:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ባለጠጎቿ ግፈኞች፣ ሰዎቿ ሐሰተኞች ናቸው፤ ምላሳቸውም አታላይ ናት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ባለ ጠጎችዋ ግፍ ተሞልተዋል፤ በውስጧ የሚኖሩትም ሐሰት ተናግረዋል፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ አታላይ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ሀብታሞቻችሁ በግፍ የተሞሉ ናቸው፤ የከተማይቱ ነዋሪዎችም ሐሰትን ይናገራሉ፤ በአንደበቶቻቸውም ይሸነግላሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ባለ ጠጎችዋን ግፍ ሞልቶባቸዋል፥ በእርስዋም የሚኖሩ በሐሰት ተናግረዋል፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ተንኰለኛ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ባለ ጠጎችዋን ግፍ ሞልቶባቸዋል፥ በእርስዋም የሚኖሩ በሐሰት ተናግረዋል፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ተንኰለኛ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ሚክያስ 6:12
29 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ሆይ፤ ከሐሰተኛ ከንፈር፣ ከአታላይ ምላስም አድነኝ።


የሰላም ንግግር ከአፋቸው አይወጣም፤ ዳሩ ግን በምድሪቱ በጸጥታ በሚኖሩት ላይ፣ ነገር ይሸርባሉ።


ነገር ግን በአፋቸው ሸነገሉት፤ በአንደበታቸው ዋሹት።


ገዥዎችሽ ዐመፀኞችና የሌባ ግብረ ዐበሮች ናቸው፤ ሁሉም ጕቦን ይወድዳሉ፤ እጅ መንሻንም በብርቱ ይፈልጋሉ፤ አባት ለሌላቸው አይቆሙም፤ የመበለቶችንም አቤቱታ አይሰሙም።


ኢየሩሳሌም ተንገዳግዳለች፤ ይሁዳም ለመውደቅ ተቃርባለች፤ ንግግራቸውም ሆነ ድርጊታቸው እግዚአብሔርን የሚቃወም፣ የክብሩንም መገኘት የሚያቃልል ነውና።


የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔር የወይን ቦታው የእስራኤል ቤት ነው፤ የይሁዳ ሰዎችም የደስታው አትክልት ናቸው። ፍትሕን ፈለገ፤ ነገር ግን ደም ማፍሰስን አየ፤ ጽድቅን ፈለገ፤ ነገር ግን የጭንቅን ጩኸት ሰማ።


ምላሳቸው የሚገድል ቀስት ነው፤ በሽንገላ ይናገራል፤ ሁሉም ከባልንጀራው ጋራ በሰላም ይናገራል፤ በልቡ ግን ያደባበታል።


እስራኤልን በምፈውስበት ጊዜ፣ የኤፍሬም ኀጢአት፣ የሰማርያም ክፋት ይገለጣል። እነርሱ ያጭበረብራሉ፤ ሌቦች ቤቶችን ሰብረው ይገባሉ፤ ወንበዴዎችም በየመንገድ ይዘርፋሉ።


ወዮ ለእነርሱ፤ ከእኔ ርቀው ሄደዋልና! ጥፋት ይምጣባቸው! በእኔ ላይ ዐምፀዋልና። ልታደጋቸው ፈለግሁ፤ እነርሱ ግን በእኔ ላይ ሐሰት ይናገራሉ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የይሁዳ ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም፤ የእግዚአብሔርን ሕግ ንቀዋል፤ ትእዛዙንም አልጠበቁምና፤ አባቶቻቸው በተከተሏቸው አማልክት፣ በሐሰት አማልክት በመመራት ስተዋልና።


በዝኆን ጥርስ ባጌጠ ዐልጋ ላይ ለምትተኙ፤ በድንክ ዐልጋችሁ ላይ ለምትዝናኑ፣ ከበጎች መንጋ ጠቦትን፣ ከሠቡትም ጥጃን ለምትበሉ፤


በዚያ ቀን፣ በመድረኩ ላይ የሚዘልሉትን ሁሉ፣ የአማልክታቸውን ቤት፣ በዐመፅና በማጭበርበር የሚሞሉትን እቀጣለሁ።”


ሹሞቿ የሚያገሡ አንበሶች፣ ገዦቿ ለነገ የማይሉ፣ የምሽት ተኵላዎች ናቸው።


አይሁድም ነገሩ እንደ ተባለው መሆኑን በመደገፍ በክሱ ተባበሩ።


“ጕረሯቸው የተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸው ይሸነግላሉ።” “በከንፈሮቻቸው የእባብ መርዝ አለ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos