Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ማቴዎስ 28:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 አሁንም ፈጥናችሁ ሂዱና ለደቀ መዛሙርቱ፣ ‘ከሙታን ተነሥቷል፤ ቀድሟችሁ ወደ ገሊላ ይሄዳል፤ በዚያ ታዩታላችሁ’ ብላችሁ ንገሯቸው። እንግዲህ ነግሬአችኋለሁ!”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ፈጥናችሁ ሂዱና ‘ከሙታን ተነሥቶአል፤ እነሆ ወደ ገሊላ ቀድሞአችሁ ይሄዳል፤ በዚያም ታዩታላችሁ’ ብላችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ንገሩአቸው። እነሆ ነግሬአችኋለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እንግዲህ በፍጥነት ሄዳችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ‘ከሞት ተነሥቶአል! እነሆ፥ ወደ ገሊላ ቀድሞአችሁ ይሄዳል፤ በዚያ ታገኙታላችሁ!’ ብላችሁ ንገሩአቸው፤ እነሆ፥ ነግሬአችኋለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ፈጥናችሁም ሂዱና ‘ከሙታን ተነሣ፤ እነሆም፥ ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል በዚያም ታዩታላችሁ፤’ ብላችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ንገሩአቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ፈጥናችሁም ሂዱና፦ ከሙታን ተነሣ፥ እነሆም፥ ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል በዚያም ታዩታላችሁ ብላችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ንገሩአቸው።

Ver Capítulo Copiar




ማቴዎስ 28:7
20 Referencias Cruzadas  

አትፍሩ፤ አትደንግጡ፤ ይህን አልነገርኋችሁምን? ቀድሞስ አላሳወቅኋችሁምን? ለዚህ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ። ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አለን? ፈጽሞ! ወይም ሌላ ዐለት አለ? የለም! ማንንም አላውቅም።”


ጕዳያችሁን ተናገሩ፤ አቅርቡ፤ ተሰብስበውም ይማከሩ። ይህን አስቀድሞ ማን ዐወጀ? ከጥንትስ ማን ተናገረ? እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን? ጻድቅና አዳኝ የሆነ አምላክ፣ ከእኔ በቀር ማንም የለም፤ ከእኔ ሌላ አምላክ የለም።


እነሆ፤ አስቀድሜ ነግሬአችኋለሁ።


ነገር ግን ከተነሣሁ በኋላ ቀድሜአችሁ ወደ ገሊላ እሄዳለሁ።”


ኢየሱስም፣ “አትፍሩ፤ ሂዱና ወደ ገሊላ እንዲሄዱ ለወንድሞቼ ንገሯቸው፤ በዚያ ያዩኛል” አላቸው።


ሴቶቹም በፍርሀትና በደስታ ተሞልተው ለደቀ መዛሙርቱ ለመንገር በፍጥነት እየሮጡ የመቃብሩን ስፍራ ትተው ሄዱ።


ከተነሣሁ በኋላ ግን፣ ቀድሜአችሁ ወደ ገሊላ እሄዳለሁ።”


እርሷም ሄዳ፣ ከርሱ ጋራ የነበሩት እያዘኑ ሲያለቅሱ አግኝታ ነገረቻቸው፤ እነርሱ ግን


እነርሱም ተመልሰው ይህንኑ ለቀሩት ነገሯቸው፤ ይሁን እንጂ እነርሱንም አላመኗቸውም።


“እነርሱም ጌታ በርግጥ ተነሥቷል! ለስምዖንም ታይቷል” ይባባሉ ነበር።


የተናገርሁት ሲፈጸም እንድታምኑ፣ ከመሆኑ በፊት አሁን ነግሬአችኋለሁ።


አስቀድሜ ይህን የነገርኋችሁ ጊዜው ሲደርስ እንድታስታውሱ ነው፤ ከእናንተ ጋራ ስለ ነበርሁ፣ ይህን ከመጀመሪያው አልነገርኋችሁም።


ተቀበረ፤ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ተጻፈውም በሦስተኛው ቀን ተነሣ፤


ከዚያም በኋላ ከዐምስት መቶ በላይ ለሚሆኑ ወንድሞች በአንድ ጊዜ ታየ፤ ከእነዚህም አብዛኛዎቹ በሕይወት አሉ፤ አንዳንዶቹ ግን አንቀላፍተዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos