Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ማቴዎስ 21:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ትቷቸው ከከተማው ወጣ፤ ወደ ቢታንያም ሄዶ በዚያው ዐደረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ትቶአቸውም ከከተማ ወጥቶ ወደ ቢታንያ ሄደ፤ በዚያም አደረ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ትቶአቸውም ከከተማ ወጥቶ ቢታንያ ወደምትባል መንደር ሄደ፤ በዚያም ዐደረ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ትቶአቸውም ከከተማ ወደ ቢታንያ ወጣ፤ በዚያም አደረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ትቶአቸውም ከከተማ ወደ ቢታንያ ወጣ በዚያም አደረ።

Ver Capítulo Copiar




ማቴዎስ 21:17
16 Referencias Cruzadas  

ቢታንያ ከኢየሩሳሌም ዐሥራ ዐምስት ምዕራፍ ያህል ትርቅ ነበር።


በማርያምና በእኅቷ በማርታ መንደር በቢታንያ ይኖር የነበረው አልዓዛር ታምሞ ነበር።


ከዚህ በኋላ እስከ ቢታንያ ይዟቸው ወጣ፤ እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው።


ኢየሱስም ኢየሩሳሌም ደረሰ፤ ከዚያም ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፤ በዙሪያው ያለውንም ሁሉ ተመለከተ፤ ቀኑም ስለ መሸ ከዐሥራ ሁለቱ ጋራ ወደ ቢታንያ ወጣ።


በመሸም ጊዜ ከከተማዪቱ ወጥተው ሄዱ።


ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይፈልጋል፤ ነገር ግን ከዮናስ ምልክት በቀር ሌላ ምልክት አይሰጠውም።” ከዚያም ኢየሱስ ትቷቸው ሄደ።


ደብረ ዘይት በተባለው ተራራ ወደሚገኙት፣ ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ ከተሞች በቀረበ ጊዜ፣ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን እንዲህ ሲል ላካቸው፤


ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ መንገድ ሲሄዱ፣ ኢየሱስ ወደ አንድ መንደር ገባ፤ ማርታ የተባለች አንዲት ሴትም በቤቷ ተቀበለችው።


ወደ ኢየሩሳሌም በደብረ ዘይት ተራራ አጠገብ ወዳሉት ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ በቀረቡ ጊዜ፣ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን እንዲህ በማለት ላካቸው፤


ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ወደ ባሕሩ ሄደ፤ ከገሊላ የመጣ እጅግ ብዙ ሕዝብም ተከተለው፤


ኢየሱስ በቢታንያ በለምጻሙ በስምዖን ቤት ሳለ፣


ልጆችን ቢያሳድጉ እንኳ፣ ልጅ አልባ እስኪሆኑ ድረስ እነጥቃቸዋለሁ፤ ፊቴን ከእነርሱ በመለስሁ ጊዜ፣ ወዮ ለእነርሱ!


ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ተጠንቀቂ፤ አለዚያ ከአንቺ ዘወር እላለሁ፤ ማንም ሊኖርባት እስከማይችል ድረስ፣ ምድርሽን ባዶ አደርጋለሁ።”


እርሱም በቢታንያ በለምጻሙ ስምዖን ቤት በማእድ ተቀምጦ ሳለ፣ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ ንጹሕ የናርዶስ ሽቱ የተሠራ የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ መጣች፣ ብልቃጡንም ሰብራ ሽቱውን በራሱ ላይ አፈሰሰችው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios