Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሉቃስ 22:56 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

56 አንዲት የቤት ሠራተኛም ጴጥሮስ እሳቱ አጠገብ ተቀምጦ አየችውና ትኵር ብላ በመመልከት፣ “ይህ ሰው ደግሞ ከርሱ ጋራ ነበረ” አለች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

56 በብርሃኑም በኩል ተቀምጦ ሳለ አንዲት አገልጋይ አየችውና ትኩር ብላ “ይህም እኮ ከእርሱ ጋር ነበረ፤” አለች።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

56 ጴጥሮስ በእሳቱ አጠገብ ተቀምጦ ሳለ አንዲት ገረድ በእሳቱ ብርሃን አየችው፤ ወደ እርሱ ትኲር ብላ ተመልክታም “ይህም ከኢየሱስ ጋር ነበር!” አለች።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

56 በእ​ሳ​ቱም ብር​ሃን በኩል ተቀ​ምጦ ሳለ አን​ዲት ብላ​ቴና አየ​ችው፤ እርሱ መሆ​ኑ​ንም ለየ​ች​ውና፥ “ይህም ከእ​ርሱ ጋር ነበር” አለች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

56 በብርሃኑም በኩል ተቀምጦ ሳለ አንዲት ገረድ አየችውና ትኵር ብላ፦ ይህ ደግሞ ከእርሱ ጋር ነበረ አለች።

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 22:56
8 Referencias Cruzadas  

ከዚህ በኋላ ጴጥሮስ በሊቀ ካህናቱ ግቢ ውስጥ ተቀምጦ ሳለ አንዲት የቤት ሠራተኛ ወደ እርሱ ቀርባ፣ “አንተም ከገሊላው ኢየሱስ ጋራ ነበርህ” አለችው።


በመሸም ጊዜ ኢየሱስ ከዐሥራ ሁለቱ ጋራ መጣ።


ኢየሱስ ግን እንዲህ አላቸው፤ “ተዉአት፣ ለምን ታስቸግሯታላችሁ? መልካም ነገር አድርጋልኛለች።


ኢየሱስም እንደ ገና እጆቹን በሰውየው ዐይኖች ላይ ጫነ፤ በዚህ ጊዜ ዐይኖቹ በሩ፤ ብርሃኑም ተመለሰለት፤ ሁሉንም ነገር አጥርቶ ማየት ቻለ።


ሰዎቹ በሊቀ ካህናቱ ግቢ ውስጥ እሳት አንድደው በአንድነት ተቀምጠው ሳለ፣ ጴጥሮስም ከእነርሱ ጋራ ተቀምጦ ነበር።


እርሱ ግን፣ “አንቺ ሴት፤ እኔ ዐላውቀውም” ብሎ ካደ።


በር ጠባቂዋም ጴጥሮስን፣ “አንተ ከዚህ ሰው ደቀ መዛሙርት አንዱ አይደለህምን?” አለችው። እርሱም፣ “አይደለሁም” አለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos