Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘሌዋውያን 7:37 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 እንግዲህ የሚቃጠል መሥዋዕት፣ የእህል ቍርባን፣ የኀጢአት መሥዋዕት፣ የበደል መሥዋዕት፣ የክህነት ሹመት መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት ሥርዐት ይህ ነው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል ቁርባን፥ የኃጢአትና የበደል መሥዋዕት፥ የቅድስናና የአንድነት መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 እንግዲህ ስለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ስለ እህል መባ፥ ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት፥ ስለ በደል ማስተስረያ መሥዋዕት ስለ ክህነት ሹመት መሥዋዕትና የአንድነት መሥዋዕት የሚፈጸሙትም የሥርዓት መመሪያዎች እነዚሁ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህል ቍር​ባን፥ የኀ​ጢ​አ​ትና የበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት፥ የቅ​ድ​ስ​ናና የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ሕግ ይህ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል ቁርባን፥ የኃጢአትና የበደል መሥዋዕት፥ የቅድስናና የደኅንነት መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 7:37
11 Referencias Cruzadas  

“ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉኝ ትቀድሳቸው ዘንድ የምታደርገው ይህ ነው፤ ነቀፋ የሌለባቸው አንድ ወይፈንና ሁለት አውራ በጎች ውሰድ።


“ከዚህ አውራ በግ ሥቡን፣ ላቱን፣ በሆድ ዕቃው ውስጥ ያለውን ስብ፣ የጕበቱን ሽፋን፣ ሁለቱን ኵላሊቶችና በዙሪያቸው ያለውን ሥብና ቀኙን ወርች ውሰድ፤ ይህ የክህነት አውራ በግ ነው።


እግዚአብሔር ሙሴን ጠራው፤ ከመገናኛውም ድንኳን እንዲህ ሲል ተናገረው፤


“ ‘ሰውየው ስለ ሠራው ኀጢአት በግ ለማቅረብ ዐቅሙ ካልፈቀደ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የዋኖስ ጫጩቶች የመጀመሪያውን ለኀጢአት መሥዋዕት፣ ሁለተኛውን ለሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ያቅርብ።


“አሮን ወይም ልጆቹ በተቀቡበት ዕለት ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡት ቍርባን ይህ ነው፦ የኢፍ አንድ ዐሥረኛው የላመ ዱቄት ግማሹን ለጧት፣ ግማሹን ለማታ የዘወትር የእህል ቍርባን አድርገው ያቅርቡት።


ሙሴ ለቅድስና የሚሆነውን ሌላ አውራ በግ አቀረበ፤ አሮንና ልጆቹም እጆቻቸውን በበጉ ራስ ላይ ጫኑ።


ሙሴ አውራ በጉን ዐረደ፤ ከደሙም ጥቂት ወስዶ የአሮንን ቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ የቀኝ እጁን አውራ ጣትና የቀኝ እግሩን አውራ ጣት አስነካ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos