Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘሌዋውያን 23:41 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

41 በየዓመቱም የእግዚአብሔር በዓል አድርጋችሁ ሰባት ቀን አክብሩ፤ ይህም ለልጅ ልጃችሁ የዘላለም ሥርዐት ነው፤ በሰባተኛውም ወር አክብሩት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

41 ይህንንም በዓል በየዓመቱ ሰባት ቀን ለጌታ አድርጉ፤ ለልጅ ልጃችሁ የዘለዓለም ሥርዓት አድርጋችሁ በሰባተኛው ወር ትጠብቁታላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

41 ይህንንም በዓል በየዓመቱ በሰባተኛው ወር ለሰባት ቀን ለእግዚአብሔር በደስታ አክብሩ፤ ይህም ለልጅ ልጆቻችሁ የዘለዓለም ሥርዓት ነው፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

41 በየ​ዓ​መቱ በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር ይህን በዓል ታደ​ርጉ ዘንድ ለልጅ ልጃ​ችሁ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግ ይሁ​ን​ላ​ችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

41 ይህንንም በዓል በየዓመቱ ሰባት ቀን ለእግዚአብሔር አድርጉ፤ ለልጅ ልጃችሁ የዘላለም ሥርዓት ነው፤ በሰባተኛው ወር ትጠብቁታላችሁ።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 23:41
5 Referencias Cruzadas  

ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው ድረስ፣ ዕዝራ በየዕለቱ ከእግዚአብሔር ሕግ መጽሐፍ ያነብብ ነበር። እነርሱም በዓሉን ሰባት ቀን አከበሩ፤ በስምንተኛውም ቀን በሕጉ መሠረት የተቀደሰ ጉባኤ ተደረገ።


ስጦታውን ለአምላካችሁ እስከምታቀርቡበት እስከዚያ ቀን ድረስ፣ እንጀራም ቢሆን ቈሎ ወይም እሸት አትብሉ፤ ይህም በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ለሚመጡት ትውልዶች የዘላለም ሥርዐት ነው።


በመጀመሪያው ቀን የመልካም ዛፍ ፍሬ፣ የዘንባባ ዝንጣፊ፣ የለመለመ ዛፍ ቅርንጫፍ የአኻያ ዛፍ ቅርንጫፍ ይዛችሁ ሰባት ቀን በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበላችሁ።


ሰባት ቀን ዳስ ውስጥ ተቀመጡ፤ በትውልዱ እስራኤላዊ የሆነ ሁሉ ዳስ ውስጥ ይሰንብት፤


“ ‘በሰባተኛው ወር በዐሥራ ዐምስተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ የዘወትር ሥራ አትሥሩ፤ ለእግዚአብሔርም የሰባት ቀን በዓል አክብሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos