ኢያሱ 7:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም14 “ ‘ማለዳ በየነገድ በየነገዳችሁ ሆናችሁ ቅረቡ፤ እግዚአብሔር የሚለየው ነገድ በየጐሣ በየጐሣው ሆኖ ከሕዝቡ መካከል ወደ ፊት ይወጣል፤ እንዲሁም እግዚአብሔር የሚለየው ጐሣ በየቤተ ሰቡ ሆኖ ወደ ፊት ይወጣል፤ እግዚአብሔር የሚለየው ቤተ ሰብ ደግሞ በግለ ሰብ በግለ ሰብ ሆኖ ወደ ፊት ይወጣል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ነገ ጧት በየነገዳችሁ ትቀርባላችሁ፤ ጌታም የሚለየው ነገድ በየወገኖቹ ይቀርባል፤ ጌታም የሚለየው ወገን በየቤተ ሰቦቹ ይቀርባል፤ ጌታም የሚለየው ቤተሰብ በየሰዉ ይቀርባል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ስለዚህ ነገ ጧት በየነገዳችሁ ቅረቡ፤ እግዚአብሔር የሚለየው ነገድ በየጐሣው ይቅረብ፤ እግዚአብሔር የሚለየው ጐሣ በየቤተሰቡ ይቅረብ፤ እግዚአብሔር የሚለየው ቤተሰብ በየግለሰቡ ይቅረብ፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 ነገም በየነገዳችሁ ትቀርባላችሁ፤ እግዚአብሔርም የሚለየው ነገድ በየወገኖቹ ይቀርባል፤ እግዚአብሔርም የሚለየው ወገን በየቤተ ሰቦቹ ይቀርባል፤ እግዚአብሔርም የሚለየው ቤተ ሰብ በየሰዉ ይቀርባል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 ነገም በየነገዳችሁ ትቀርባላችሁ፥ እግዚአብሔርም የሚለየው ነገድ በየወገኖቹ ይቀርባል፥ እግዚአብሔርም የሚለየው ወገን በየቤተ ሰቦቹ ይቀርባል፥ እግዚአብሔርም የሚለየው ቤተ ሰብ በየሰዉ ይቀርባል። Ver Capítulo |