Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢያሱ 22:34 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 የሮቤልና የጋድ ወገኖችም፣ እግዚአብሔር አምላክ ለመሆኑ ይህ በመካከላችን ምስክር ነው፤ በማለት መሠዊያውን “ምስክር” ብለው ጠሩት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆችም፦ “ጌታ አምላክ እንደሆነ ይህ በመካከላችን ምስክር ነው” ሲሉ መሠዊያውን ምስክር ብለው ጠሩት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 የሮቤልና የጋድ ሕዝብም “ይህ መሠዊያ እግዚአብሔር ብቻ አምላክ ስለ መሆኑ ለሁላችን ምስክር ነው” አሉ፤ ከዚህም የተነሣ “ምስክር” ብለው ጠሩት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 ኢያ​ሱም መሠ​ዊ​ያ​ውን “የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆች፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ምስ​ክር” ብሎ ጠራው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ቸው እንደ ሆነ ይህ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ምስ​ክር ነውና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆችም፦ እግዚአብሔር አምላክ እንደ ሆነ ይህ በመካከላችን ምስክር ነው ሲሉ መሠዊያውን ምስክር ብለው ጠሩት።

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 22:34
8 Referencias Cruzadas  

ላባም ክምር ድንጋዩን ይጋርሠሀዱታ ብሎ ጠራው፤ ያዕቆብ ደግሞ ገለዓድ አለው።


ላባም “ይህ ክምር ድንጋይ በእኔና በአንተ መካከል ዛሬ ምስክር ነው” አለው። ገለዓድ ተብሎ የተጠራውም በዚሁ ምክንያት ነው፤


ሕዝቡም ሁሉ ይህን ሲያዩ፣ በግንባራቸው ተደፍተው፣ “አምላክ እግዚአብሔር እርሱ እውነተኛ ነው! እግዚአብሔር እርሱ እውነተኛ አምላክ ነው!” አሉ።


በዚያ ቀን በግብጽ ምድር መካከል ለእግዚአብሔር መሠዊያ ይሠራል፤ በድንበሯም ላይ ለእግዚአብሔር ዐምድ ይቆማል።


“ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ፣ እርሱ እኔ እንደ ሆንሁ ትረዱ ዘንድ፣ እናንተ ምስክሮቼ፣ የመረጥሁትም ባሪያዬ ናችሁ” ይላል እግዚአብሔር። “ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም፤ ከእኔም በኋላ አይኖርም።


ኢየሱስም፣ “አንተ ሰይጣን ከፊቴ ራቅ! ‘ለጌታ ለአምላክህ ስገድ፤ እርሱንም ብቻ አምልክ’ ተብሎ ተጽፏል” አለው።


በሌላም በኩል የሚቃጠል መሥዋዕታችንን፣ ሌላውን ቍርባናችንንና የኅብረት መሥዋዕታችንን ይዘን በተቀደሰው ስፍራ እግዚአብሔርን እንደምናመልክ መሠዊያው በእኛና በእናንተ እንዲሁም በሚቀጥሉት ትውልዶች መካከል ምስክር ይሆናል። ስለዚህ ወደ ፊት ዘሮቻችሁ ዘሮቻችንን፣ ‘ከእግዚአብሔር ዘንድ ድርሻ የላችሁም’ ሊሏቸው አይችሉም።


ኢያሱም ሕዝቡን ሁሉ፣ “እነሆ፤ ይህ ድንጋይ፣ እግዚአብሔር የተናገረንን ሁሉ ሰምቷል፣ በእኛም ይመሰክርብናል፤ እናንተም በአምላካችሁ ዘንድ እውነተኞች ሆናችሁ ባትገኙ ምስክር ይሆንባችኋል” አላቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos